ዮሐንስ 13:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔር ስለ እርሱ የከበረ ከሆነ፥ እግዚአብሔር ደግሞ እርሱን ራሱን ያከብረዋል፤ ወዲያውም ያከብረዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ እግዚአብሔር በርሱ ከከበረ፣ እግዚአብሔር ልጁን በራሱ ዘንድ ያከብረዋል፤ ወዲያውም ያከብረዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር በእርሱ አማካይነት ከከበረ እግዚአብሔርም እርሱን ያከብረዋል፤ ሳይዘገይም ያከብረዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር በእርሱ ከከበረ እግዚአብሔርም እርሱን ያከብረዋል፥ ያንጊዜም ያከብረዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር ስለ እርሱ የከበረ ከሆነ፥ እግዚአብሔር ደግሞ እርሱን ራሱን ያከብረዋል ወዲያውም ያከብረዋል። |