ዮሐንስ 11:36 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህም አይሁድ “እንዴት ይወደው እንደ ነበረ እዩ፤” አሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አይሁድም፣ “እንዴት ይወድደው እንደ ነበር አያችሁ!” አሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ አይሁድ “እንዴት ይወደው እንደ ነበረ ተመልከቱ” አሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አይሁድም፥ “ምን ያህል ይወደው እንደ ነበር እዩ” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ አይሁድ፦ “እንዴት ይወደው እንደ ነበረ እዩ” አሉ። |
ክርስቶስም እንዳፈቀራችሁ፥ ስለ እናንተም ለእግዚአብሔር መልካም መዓዛ ያለው መባንና መሥዋዕት አድርጎ ራሱን አሳልፎ እንደሰጠ፥ በፍቅር ተመላለሱ።
የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን እንድንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደ ሰጠን እዩ፤ እንዲሁም ነን። ዓለም እርሱን ስላላወቀው እኛንም አያውቀንም።
እንዲሁም ከታመነው ምስክር፥ ከሙታን በኩር ከሆነው፥ የምድርም ነገሥታት ገዥ ከሆነው ከኢየሱስ ክርስቶስ፤ ለወደደን፥ ከኀጢአታችንም በደሙ ላጠበን፥