ኢዮብ 6:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በየዳርቻቸውም የሚሄዱ ነጋዴዎች ፈቀቅ ይላሉ፥ ወደ በረሃ ወጥተው ይጠፋሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሲራራ ነጋዴዎች ውሃ አጥተው መንገዳቸውን ይቀይራሉ፤ ወደ በረሓም ገብተው ይጠፋሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጭነት ከብቶችን እየነዱ የሚሄዱ መንገደኞች ከመንገድ ወጥተው ውሃ ፍለጋ ወደ በረሓ ገብተው ባዝነው ይጠፋሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደዚሁም እኔ ከሁሉ ተለይቼ ጠፋሁ፥ ከቤቴም ወጥቼ የተጣልሁ ሆንሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በየዳርቻቸውም የሚሄዱ ነጋዴዎች ፈቀቅ ይላሉ፥ ወደ በረሃ ወጥተው ይጠፋሉ። |