ኤርምያስ 8:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኀዘኔ የማይጽናና ነው፥ ልቤም በውስጤ ደክሞአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሐዘኔ የምታጽናናኝ ሆይ፤ ልቤ በውስጤ ዝላለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መጽናናት የማይገኝለት ብርቱ ሐዘን ደርሶብኛል፤ ልቤም እጅግ ዝሎአል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልባችሁን ታምማችሁ ትቅበዘበዛላችሁ። ከሚያቅበዘብዝ የልብ ሕመማችሁ የሚያድናችሁ የለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኀዘኔ የማይጽናና ነው፥ ልቤም በውስጤ ደክሞአል። |
ስለ ነቢያት፤ ልቤ በውስጤ ተሰብሮአል አጥንቶቼም ሁሉ ታውከዋል፤ ከጌታ የተነሣ፥ ከቅዱስ ቃላቱም የተነሣ የወይን ጠጅ እንዳሸነፈው እንደ ሰካራም ሰው ሆኛለሁ።
አንጀቴ! አንጀቴ! ልቤ በጣም ታምሞአል፥ በውስጤም ልቤ ታውኮብኛል፤ ነፍሴ ሆይ! የመለከትን ድምፅና የጦርነትን ሁካታ ሰምተሻልና ዝም ማለት አልችልም።
እኔ ሰምቻለሁ፥ አንጀቴ ራደብኝ፥ ከድምፁ የተነሣ ከንፈሮቼ ተንቀጠቀጡ፤ መበስበስ ወደ አጥንቶቼ ውስጥ ገባ፥ በውስጤም ተንቀጠቀጥሁ፥ በአስጨነቁን ሕዝብ ላይ እስኪመጣ ድረስ፥ የመከራን ቀን ዝም ብዬ እጠብቃለሁ።