ኤርምያስ 6:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የተዋበችውንና የተቀማጠለችውን የጽዮንን ልጅ አጐሳቁላለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ውብና ሽሙንሙን የሆነችዋን፣ የጽዮንን ሴት ልጅ አጠፋታለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ውብና አስደሳች የሆነችው የጽዮን ከተማ ትጠፋለች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቅምጥል የጽዮን ልጅ ሆይ! ውበትሽ ይጐሳቈላል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የተዋበችውንና የተሰባቀለችውን የጽዮንን ልጅ አጐሰቍላለሁ። |
እንደታመመች የበኩርዋንም እንደምትወልድ ሴት የጭንቀት ድምፅ ሰምቻለሁና፤ የጽዮን ሴት ልጅ ድምፅ በድካም ታቃስታለች፥ እጆችዋንም በመዘርጋት፦ “በነፍሰ ገዳዮች ፊት ነፍሴ ዝላለችና ወዮልኝ!” አለች።
አሌፍ። ጌታ በቁጣው የጽዮንን ሴት ልጅ እንደምን አደመናት! የእስራኤልን ውበት ከሰማይ ወደ ምድር ጣለ፥ በቁጣውም ቀን የእግሩን መረገጫ አላሰበም።
ሜም። የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ሆይ፥ ምን እመሰክርልሻለሁ? በምንስ እመስልሻለሁ? ድንግሊቱ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ አጽናናሽ ዘንድ በምን አስተካክልሻለሁ? ስብራትሽ እንደ ባሕር ታላቅ ነውና፥ የሚፈውስሽ ማን ነው?
በመካከልህ ተለሳልሳና ተቀማጥላ የምትኖር፥ ከልስላሴና ከቅምጥልነት የተነሣ እግሮችዋ ዐፈር ነክቶት የማያውቁ ሴት ዐቅፋው ለምትተኛው ባሏና በገዛ ወንድ ወይም ሴት ልጆችዋ ላይ ትከፋለች።