ኤርምያስ 38:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አለቆቹ ግን እኔ ከአንተ ጋር እንደተነጋገርሁ ቢሰሙ፥ ወደ አንተም መጥተው፦ ‘ለንጉሡ ያልኸው ምንድነው? ንገረን አትሸሽገንም፥ እኛም አንገድልህም፤ ንጉሡስ ለአንተ ምን አለህ?’ ንገረን ቢሉህ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም መኳንንቱ ከአንተ ጋራ እንደ ተነጋገርሁ ሰምተው ወደ አንተ ቢመጡና፣ ‘ንጉሡን ምን እንዳልኸው፣ ንጉሡም ምን እንዳለህ ንገረን፤ ሳትደብቅ ንገረን፤ አለዚያ እንገድልሃለን’ ቢሉህ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባለ ሥልጣኖቹ እኔ ከአንተ ጋር መነጋገሬን የሰሙ እንደ ሆነ መጥተው ምን እንደ ተባባልን ይጠይቁሃል፤ ሁሉን ነገር ባትነግራቸው እንገድልሃለን ብለው ያስፈራሩሃል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አለቆቹ ግን እኔ ከአንተ ጋር እንደ ተነጋገርሁ ቢሰሙ፥ ወደ አንተም መጥተው፦ ለንጉሡ ያልኸውን ንገረን፤ አትሸሽገንም፤ እኛም አንገድልህም፤ ደግሞ ንጉሡ ያለህን ንገረን ቢሉህ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አለቆቹ ግን እኔ ከአንተ ጋር እንደ ተነጋገርሁ ቢሰሙ፥ ወደ አንተም መጥተው፦ ለንጉሡ ያልኸውን ንገረን አትሸሽገንም፥ እኛም አንገድልህም፥ ደግሞ ንጉሡ ያለህን ንገረን ቢሉህ፥ አንተ፦ |
አለቆቹም ሁሉ ወደ ኤርምያስ መጥተው ጠየቁት፥ እርሱም ንጉሡ እንዳዘዘው እነዚህን ሁሉ ቃላት ነገራቸው። ነገሩም አልተሰማም ነበርና ከእርሱ ጋር መነጋገርን ተዉ።