ኤርምያስ 25:37 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከጌታ ጽኑ ቁጣ የተነሣ የሰላም በረት ፈርሶአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእግዚአብሔር ጽኑ ቍጣ የተነሣ፣ ሰላማዊው ምድር ባድማ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእግዚአብሔር ኀይለኛ ቊጣ ምክንያትም ሰላማዊው መኖሪያቸው ፈራርሶአል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእግዚአብሔር ጽኑ ቍጣ የተነሣ የሰላም ውበት ፈርሶአል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእግዚአብሔር ጽኑ ቍጣ የተነሣ የሰላም በረት ፈርሶአል። |
አዳራሹ ወና ይሆናል፥ በሰው የተጨናነቀውም ከተማ ወና ይሆናል፤ ምሽጉና ግንቡም ለዘለዓለም ዋሻ፥ የምድረ በዳም አህያ ደስታ፥ የመንጎችም ማሰማርያ ይሆናል።
መከርህንና እንጀራህን ይበላሉ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህንም ይበሉአቸዋል፤ በጎችህንና ላሞችህንም ይበላሉ፤ ወይንህንና በለስህንም ይበላሉ፤ የምትተማመንባቸውን የተመሸጉ ከተሞችን በሰይፍ ይደመስሳሉ።