ኤርምያስ 20:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በነጋውም ጳስኮር ኤርምያስን ከመንቈር ውስጥ ፈታው። ኤርምያስም እንዲህ አለው፦ “ጌታ ስምህን፦ ማጎርሚሳቢብ እንጂ ጳስኮር ብሎ አይጠራህም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በማግስቱም ጳስኮር ኤርምያስን ከተጠረቀበት ግንድ አወጣው፤ ኤርምያስም እንዲህ አለው፤ “እግዚአብሔር ከእንግዲህ ማጎርሚሳቢብ ብሎ ይጠራሃል እንጂ ጳስኮር አይልህም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በማግስቱም ከሰንሰለት እስራት ከፈታኝ በኋላ እንዲህ አልኩት፥ “ከእንግዲህ ወዲህ እግዚአብሔር ስምህን ፓሽሑር ብሎ አይጠራህም፤ ለአንተ ያወጣልህ ስም ‘ሽብር በየስፍራው’ የሚል ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በነጋውም ጳስኮር ኤርምያስን ከአዘቅት ውስጥ አወጣው። ኤርምያስም እንዲህ አለው፥ “እግዚአብሔር ስምህን፦ ዘዋሪ ስደተኛ እንጂ ጳስኮር ብሎ አይጠራህም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በነጋውም ጳስኮር ኤርምያስን ከግንድ ውስጥ አወጣው። ኤርምያስም እንዲህ አለው፦ እግዚአብሔር ስምህን፦ ማጎርሚሳቢብ እንጂ ጳስኮር ብሎ አይጠራህም። |
ሰውየውም፦ “ከእንግዲህ ወዲህ ስምህ ያዕቆብ አይባልም፤ ነገር ግን ከእግዚአብሔር ከሰውም ጋር ታግለህ አሸንፈሃልና እስራኤል ይባላል” አለው።
የብዙ ሰዎችን የክፋት ሹክሹክታ ሰምቻለሁ፥ ማስፈራራትም ከብቦኛል። መውደቄን የሚጠብቁ የሰላሜ ሰዎች ሁሉ፦ “ምናልባት ይታለል እንደሆነ፥ እናሸንፈውም እንደሆነ፥ እርሱንም እንበቀል እንደሆነ፥ ክሰሱት እኛም እንከስሰዋለን” ይላሉ።
ፈርተው ወደ ኋላ ሲመለሱ፥ ኃያላኖቻቸውም ሲደበደቡ ወደ ኋላቸውም ሳይመለከቱ ፈጥነው ሲሸሹ ለምን አየሁ? በዚህና በዚያ ድንጋጤ አለ፥ ይላል ጌታ።
ስለዚህ፥ እነሆ፥ ስፍራ ከመታጣቱ የተነሣ በቶፌት ይቀበራሉና የእርድ ሸለቆ ይባላል እንጂ ቶፌት ወይም የሄኖም ልጅ ሸለቆ ዳግመኛ የማይባልበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል ጌታ።
ታው። እንደ በዓል ቀን የሚያስፈሩኝን ከዙሪያዬ ጠራህ፥ በእግዚአብሔር ቁጣ ቀንም ያመለጠ ወይም የቀረ አልተገኘም፥ ያቀማጠልኋቸውንና ያሳደግኋቸውን ጠላቴ በላቸው።
እጄ ከንቱ ራእይን በሚያዩ፥ በውሸትም በሚያምዋርቱ ነቢያት ላይ ትሆናለች፥ እነርሱም በሕዝቤ ማኅበር ውስጥ አይገኙም፥ በእስራኤል ቤት መዝገብ አይጻፉም፥ ወደ እስራኤልም ምድር አይገቡም፥ በዚያን ጊዜ እኔ ጌታ እግዚአብሔር እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።