ኤርምያስ 1:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም እጁን ዘርግቶ አፌን ዳሰሰ፥ እንዲህም አለኝ፦ “እነሆ፥ ቃሎቼን በአፍህ ውስጥ አኑሬአለሁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም እጁን ዘርግቶ አፌን ዳሰሰና እንዲህ አለኝ፤ “እነሆ፤ ቃሌን በአፍህ አኑሬአለሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር እጁን ዘርግቶ ከንፈሮቼን ዳሰሰ፤ እንዲህም አለኝ፦ “እነሆ የምትናገረውን ቃሌን ሰጥቼሃለሁ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም እጁን ዘርግቶ አፌን ዳሰሰ፥ እግዚአብሔርም አለኝ፥ “እነሆ፥ ቃሌን በአፍህ ውስጥ አኑሬአለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም እጁን ዘርግቶ አፌን ዳሰሰ፥ እግዚአብሔርም፦ እነሆ፥ ቃሌን በአፍህ ውስጥ አኑሬአለሁ፥ |
የደከመውን በቃል እንዴት እንደምደግፍ እንዳውቅ ጌታ እግዚአብሔር የተማሩትን ምላስ ሰጥቶኛል፤ ማለዳ ማለዳ ያነቃኛል፥ እንደ ተማሪዎችም እንድትሰማ ጆሮዬን ያነቃቃል።
ከእነርሱ ጋር ያለው ቃል ኪዳኔ ይህ ነው ይላል ጌታ፤ በአንተ ላይ ያለው መንፈሴ በአፍህም ውስጥ ያደረግሁት ቃሌ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለዓለም ድረስ ከአፍህ፥ ከዘርህም አፍ፥ ከዘር ዘርህም አፍ አይለይም፥ ይላል ጌታ።
ስለዚህ ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ብትመለስ እመልስሃለሁ በፊቴም ትቆማለህ፤ የከበረውንም ከተዋረደው ብትለይ እንደ አፌ ትሆናለህ፤ እነርሱ ወደ አንተ ይመለሳሉ፥ አንተ ግን ወደ እነርሱ አትመለስም።
“አንድ የመጽሐፍ ክርታስ ውሰድ፥ ለአንተም ከተናገርሁበት ቀን፥ ከኢዮስያስ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በእስራኤልና በይሁዳ ላይ፥ በአሕዛብም ሁሉ ላይ ለአንተ የተናገርሁትን ቃላት ሁሉ ጻፍበት።
ስለዚህም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ይህን ቃል ተናግራችኋልና እነሆ፥ በአፍህ ውስጥ ቃሌን እሳት፥ ይህንም ሕዝብ እንጨት አደርጋለሁ፥ ትበላቸዋለችም።
በኮሬብ ጉባኤ በተደረገበት ዕለት፥ ‘እንዳልሞት የጌታ የእግዚአብሔርን ድምፅ አልስማ፤ እንዲህ ያለውንም አስፈሪ እሳት ደግሜ አልይ’ ብለህ አምላክህን ጌታን የጠየቅኸው ይህን ነውና።