በዚያም ቀን ለተወደደው የወይን ቦታ ተቀኙለት።
በዚያ ቀን እንዲህ ይባላል፤ “ለመልካሙ የወይን ቦታ ዘምሩለት፤
በዚያን ጊዜ ፍሬአማ ለሆነው የወይን ተክል ቦታ ዘምሩለት፤
በዚያም ቀን ለተወደደው የወይን ቦታ ተቀኙለት።
እኔ የተመረጠች ወይን ፍጹምም እውነተኛ ዘር አድርጌ ተክዬሽ ነበር፤ አንቺ ግን የተበላሸ የእንግዳ ወይን ግንድ ሆነሽ እንዴት ተለወጥሽብኝ?
በዚያም ጊዜ እስራኤል ይህን መዝሙር ዘመረ፦ አንተ ምንጭ ሆይ! ፍለቅ፤ እናንተም ዘምሩለት፤