ዘፍጥረት 7:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጥፋትም ውኃ በምድር ላይ አርባ ቀን አላቋረጠም፥ ውኃውም በዛ፥ መርከቢቱንም አነሣ፥ ከምድርም በላይ ከፍ አለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጥፋት ውሃም ለአርባ ቀናት ያለ ማቋረጥ በምድር ላይ ዘነበ፤ ውሃው እየጨመረ በሄደ መጠን መርከቧን ከምድር ወደ ላይ አነሣት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጥፋት ውሃ አርባ ቀን ድረስ በመዝነብ እየበረታ ሄደ፤ የውሃውም ጥልቀት እየጨመረ ስለ ሄደ መርከቡን ከምድር በላይ ከፍ አደረገው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጥፋት ውኃ በምድር ላይ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ነበረ፤ ውኃውም በዛ፤ መርከቢቱንም አነሣ፤ ከምድርም ወደ ላይ ከፍ ከፍ አለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጥፋትም ውኂ በምድር ላይ አርባ ቀን ነበረ ውኂውም በዛ መርከቢቱንም አነሣ ከምድርም ወደ ላይ ከፍ ከፍ አለች። |
አዳራሹን በሰማይ የሠራ፥ ጠፈሩንም በምድር ላይ የመሠረተ፥ የባሕርንም ውኃ ጠርቶ በምድር ፊት ላይ የሚያፈስሰው እርሱ ነው፤ ስሙም ጌታ ነው።