ዘፍጥረት 48:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደግሞም፦ ‘እነሆ ፍሬያማ አደርግሃለሁ፥ አበዛሃለሁም፥ ለብዙም ሕዝብ ጉባኤ አደርግሃለሁ፥ ይህችንም ምድር ከአንተ በኋላ ለዘለዓለም ርስት ለዘርህ እሰጣታለሁ።’” አለኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህም አለኝ፤ ‘ፍሬያማ አደርግሃለሁ፣ አበዛሃለሁ፣ ለብዙ ሕዝብም ጉባኤ አደርግሃለሁ፤ ይህችንም ምድር ከአንተ በኋላ ለሚነሡ ዘሮችህ የዘላለም ርስት አድርጌ እሰጣቸዋለሁ።’ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደግሞም ‘ዘርህን አበዛለሁ፤ ተወላጆችህም ብዙ ሕዝቦች ይሆናሉ፤ ይህችንም ምድር ከአንተ በኋላ ለሚመጡት ዘሮችህ ለዘለዓለም ርስት አድርጌ እሰጣቸዋለሁ’ አለኝ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም አለኝ፦ እነሆ፥ አበዛሃለሁ፤ አባዛሃለሁም፤ ለብዙም ሕዝብ ጉባኤ አደርግሃለሁ፤ ይህችንም ምድር ለአንተ፥ ከአንተም በኋላ ለዘለዓለም ርስት ለዘርህ እሰጣታለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ ፍሬያማ አደርግሃለሁ አበዛሃልሁም ለብዙም ሕዝብ ጉባኤ አደርግሃለው ይህችንም ምድር ከአንተ በኍላ ለዘላለም ርስት ለዘርህ እሰጣታለሁ። |
በእንግድነት የምትኖርባትን ምድር፥ የከነዓን ምድር ሁሉ፥ ለዘለዓለም ግዛት ይሆንህ ዘንድ ለአንተና ከአንተ በኋላ ለዘርህ እሰጣለሁ፥ አምላክም እሆናቸዋለሁ።”
በእውነት መባረክን እባርክሃለሁ፥ ዘርህንም እንደ ሰማይ ከዋክብት እና በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ አበዛዋለሁ፤ ዘሮችህም የጠላቶችን ደጅ ይወርሳሉ፥
እግዚአብሔርም አለው፦ “ሁሉን ቻይ አምላክ እኔ ነኝ፥ ብዛ፥ ተባዛም፥ ሕዝብና የአሕዛብ ማኅበር ከአንተ ይሆናል፥ ነገሥታትም ከጉልበትህ ይወጣሉ።
ለአገልጋዬ ለያዕቆብ በሰጠኋት፥ አባቶቻችሁም በኖሩባት ምድር ይኖራሉ፤ እነርሱ፥ ልጆቻቸውና የልጅ ልጆቻቸው ለዘለዓለም በእርሷ ይኖራሉ፤ አገልጋዬ ዳዊት ለዘለዓለም ልዑላቸው ይሆናል።