እንዲህም ሆነ፥ ይስሐቅ ሸምግሎ ዐይኖቹ ከማየት በፈዘዙ ጊዜ ታላቁን ልጁን ዔሳውን ጠርቶ፥ “ልጄ ሆይ፥” አለው እርሱ፥ “እነሆ አለሁ” አለው።
ዘፍጥረት 48:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤልም ዐይኖች ከሽምግልና የተነሣ ደክመው ነበር፥ ማየትም አይችልም ነበር፥ ወደ እርሱም አቀረባቸው፥ ሳማቸውም፥ አቀፋቸውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ እስራኤል ዐይኖቹ በእርጅና ምክንያት በመድከማቸው አጥርቶ ማየት ይሳነው ነበር፤ ስለዚህ ዮሴፍ ልጆቹን አባቱ ዘንድ አቀረባቸው፤ አባቱም ስሞ ዐቀፋቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የያዕቆብ ዐይኖች በእርጅናው ምክንያት ስለ ደከሙ አጥርቶ ማየት አይችልም ነበር፤ ስለዚህ ዮሴፍ ልጆቹን ወደ እርሱ አቀረበለት፤ እርሱም ዕቅፍ አድርጎ ሳማቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም ዐይኖች ከሽምግልና የተነሣ ከብደው ነበር፤ ማየትም አይችልም ነበር፤ ወደ እርሱም አቀረባቸው፤ ሳማቸውም፤ አቀፋቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ዓይኖች ከሸምግልና የተነሣ ከብደው ነበር። ማየትም አይችልም ነበር ወደ እርሱም አቀረባቸው ሳማቸውም አቀፋቸውም። |
እንዲህም ሆነ፥ ይስሐቅ ሸምግሎ ዐይኖቹ ከማየት በፈዘዙ ጊዜ ታላቁን ልጁን ዔሳውን ጠርቶ፥ “ልጄ ሆይ፥” አለው እርሱ፥ “እነሆ አለሁ” አለው።
በዚህ ጊዜ ኤልሳዕ በሬዎቹን ትቶ ወደ ኤልያስ በመሮጥ “አባትና እናቴን ስሜ እንድሰናበት ፍቀድልኝ ከዚያም በኋላ እከተልሃለሁ” አለው። ኤልያስም “እሺ፥ ተመልሰህ ሂድ፤ እኔ አልከለክልህም!” ሲል መለሰለት።
ቤት ጠባቆች በሚንቀጠቀጡበት፥ ኃያላን ሰዎችም በሚጎብጡበት፥ ጥቂቶች ሆነዋልና ፈጭታዎች ሥራ በሚፈቱበት፥ በመስኮትም ሆነው የሚመለከቱ በሚጨልሙበት፥ በአደባባይም ደጆቹ በሚዘጉበት ቀን፥
የዚህን ሕዝብ ልብ አደንድን፤ ጆሮአቸውን ድፈን፤ ዐይኖቻቸውንም ክደን፤ ይህ ካልሆነማ፤ በዐይናቸው አይተው፤ በጆሮአቸው ሰምተው፤ በልባቸውም አስተውለው በመመለስ ይፈወሳሉ።”