ዘፍጥረት 41:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰባቱ የሚያማምሩ ላሞች፥ ሰባት ዓመታት ናቸው፥ ሰባቱም የሚያማምሩ የእሸት ዛላዎች ሰባት ዓመታት ናቸው፤ ሕልሙም አንድና ተመሳሳይ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰባቱ የሚያማምሩ ላሞች፣ ሰባት ዓመታት ናቸው፣ ሰባቱም የሚያማምሩ የእሸት ዛላዎች ሰባት ዓመታት ናቸው፤ ሕልሙም አንድና ተመሳሳይ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰባቱ የሚያምሩ ላሞች ሰባት ዓመቶች ናቸው፤ ሰባቱም ያማሩ የእሸት ዛላዎች ሰባት ዓመቶች ናቸው፤ የሁለቱም ትርጒም አንድ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነዚያ ሰባቱ መልካካሞች ላሞች ሰባት ዓመታት ናቸው፤ እነዚያም ሰባቱ መልካካሞች እሸቶች ሰባት ዓመታት ናቸው፤ የፈርዖን ሕልሙ አንድ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰባቱ መልካካሞች ላሞች ሰባት ዓመታት ናቸው፥ ሰባቱም መልካካሞች እሸቶች ሰባት ዓመታት ናቸው ሕልሙ አንድ ነው። |
ዮሴፍም ለፈርዖን እንዲህ አለው፤ “ሁለቱም የፈርዖን ሕልሞች ተመሳሳይና አንድ ዓይነት ናቸው፤ እግዚአብሔር ወደ ፊት የሚያደርገውን ለፈርዖን ገልጦለታል።
ከእነርሱም በኋላ ዐጥንታቸው የወጣ አስከፊ መልክ ያላቸው ሰባት ላሞች፥ ሰባት ዓመታት ናቸው፤ እንደዚሁም ፍሬ አልባ የሆኑትና በምሥራቅ ነፋስ ተመትተው የደረቁት ሰባት የእሸት ዛላዎች ሰባት የራብ ዓመታት ናቸው።
ፈርዖንም እንደገና እንቅልፍ ወስዶት ሳለ፥ ሌላ ሕልም አየ። በሕልሙም በአንድ የእህል አገዳ ላይ፥ ፍሬያቸው የተንዠረገገና ያማረ ሰባት የእሸት ዛላዎች ሲወጡ አየ።