ዘፍጥረት 4:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የወንድሙም ስም ዩባል ነበረ፥ እርሱም በገናንና ዋሽንትን ለሚይዙ አባት ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወንድሙም ዩባል ይባላል፤ እርሱም የበገና ደርዳሪዎችና የዋሽንት ነፊዎች አባት ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእርሱ ወንድም ዮባልም ዋሽንትና በገና የሚጫወቱ የሙዚቀኞች አባት ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የወንድሙም ስም ኢዮቤል ነበር፤ እርሱም በገናንና መሰንቆን አስተማረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የወንድሙም ስም ዩባል ነበረ፤ እርሱም በገናንና መለከትን ለሚይዙ አባት ነበረ። |
በግብዣቸው ላይ በገናና መሰንቆ፤ ከበሮና ዋሽንት እንዲሁም የወይን ጠጅ አለ፤ ነገር ግን ለጌታ ሥራ ቦታ አልሰጡም፤ ለእጆቹም ሥራ ክብር አላሳዩም።