ዘፍጥረት 4:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ላሜሕም ሁለት ሚስቶችን አገባ፥ የአንዲቱ ስም ዓዳ፥ የሁለተኛይቱ ስም ጺላ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ላሜሕ ሁለት ሚስቶች አገባ፤ የአንደኛዋ ስም ዓዳ፣ የሁለተኛዋም ሴላ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ላሜክ ዓዳ እና ጺላ የተባሉትን ሁለት ሚስቶች አገባ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ላሜሕም ለራሱ ሁለት ሚስቶችን አገባ፤ የአንዲቱ ስም ዓዳ፥ የሁለተኛይቱ ስም ሴላ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ላሜሕም ለራሱ ሁለት ሚስቶችን አገባ፤ የአንዲቱ ስም ዓዳ፤ የሁለረኚይቱ ስም ሴላ ነበረ። |
ላሜሕም ለሚስቶቹ፥ “ዓዳ እና ጺላ፥ እስቲ አድምጡኝ፥ እናንት የላሜሕ ሚስቶች ሆይ፥ የምለውን ስሙኝ፤ ቢያቆስለኝ ጐልማሳውን ገደልኩ ብላቴናውንም ስለ መወጋቴ ገደልኩ፤