ዘፍጥረት 4:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቃየንም ጌታን አለው፦ “ኃጢአቴ ልሸከማት የማልችላት ታላቅ ናት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቃየንም እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፤ “ቅጣቴ ልሸከመው ከምችለው በላይ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቃየልም እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፤ “ይህ ቅጣት እኔ ልሸከመው ከምችለው በላይ ነው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቃየልም እግዚአብሔርን አለው፥ “ኀጢአቴ ይቅር የማትባል ታላቅ ናትን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቃየንም እግዚአብሔርን አለው፤ ኂጢአቴ ልሸከማት የማልችላት ታላቅ ናት። |
በሚዛንም አንድ ታላንት የሚያህል ታላቅ በረዶ በሰዎች ላይ ከሰማይ ወረደባቸው፤ ሰዎቹም ከበረዶው መቅሰፍት የተነሣ እግዚአብሔርን ተሳደቡ፤ መቅሰፍቱ እጅግ ታላቅ ነበርና።
ሰዎችም በታላቅ ትኩሳት ተቃጠሉ፤ በነዚህም መቅሠፍቶች ላይ ሥልጣን ያለውን የእግዚአብሔርን ስም ተሳደቡ፤ ክብርንም እንዲሰጡት ንስሓ አልገቡም።