“እጅህን ከጭኔ በታች አድርግ፥ እኔም አብሬ ከምኖራቸው ከከነዓን ሴቶች ልጆች ለልጄ ሚስት እንዳትወስድለት በሰማይና በምድር አምላክ በእግዚአብሔር አምልሃለሁ፥
ዘፍጥረት 38:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እዚያም ሳለ፥ ይሁዳ የከነዓናዊውን የሴዋን ሴት ልጅ አየ፤ እርሷንም አግብቶ አብሯት ተኛ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እዚያም ሳለ፣ ይሁዳ የከነዓናዊውን የሹዓን ሴት ልጅ አየ፤ እርሷንም አግብቶ ዐብሯት ተኛ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እዚያም ይሁዳ የከነዓናዊውን የሹዓን ሴት ልጅ አየ፤ እርስዋንም አግብቶ ወደርስዋ ገባ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚያም ይሁዳ ያንድ ከነዓናዊ ሰው ሴት ልጅን አየ፤ ስምዋም ሴዋ ይባላል። ወሰዳትም፤ ወደ እርስዋም ገባ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚያም ይሁዳ የከነዓናዊውን የሴዋን ሴት ልጅ አየ ወሰዳትም ወደ እርስዋም ገባ። |
“እጅህን ከጭኔ በታች አድርግ፥ እኔም አብሬ ከምኖራቸው ከከነዓን ሴቶች ልጆች ለልጄ ሚስት እንዳትወስድለት በሰማይና በምድር አምላክ በእግዚአብሔር አምልሃለሁ፥
ሴቲቱም ዛፉ ለመብላት ያማረ እንደሆነ፥ ለዓይንም እንደሚያስጎመጅ፥ ጥበብ ለማግኘትም የሚመኙት እንደሆነ አየች፤ ከፍሬውም ወሰደችና በላች፤ ለባልዋም ደግሞ ሰጠችው፤ እርሱም በላ።
በዚያን ዘመን ኔፊሊም በምድር ላይ ነበሩ፥ እና ከዚያም በኋላ የእግዚአብሔር ልጆች የሰውን ሴቶች ልጆች ባገቡ ጊዜ ልጆችን ወለዱላቸው፥ እነርሱም በዱሮ ዘመን፥ ስማቸው የታወቀ፥ ኃያላን ሆኑ።
አንድ ቀን ማታ፥ ዳዊት ከአልጋው ተነሥቶ በቤተ መንግሥቱ ሰገነት ወዲያና ወዲህ ይመላለስ ነበር፤ ከሰገነቱ ላይ እንዳለም፥ አንዲት ሴት ገላዋን ስትታጠብ አየ፤ ሴቲቱም እጅግ ውብ ነበረች።
የይሁዳ ልጆች፤ ዔር፥ አውናን፥ ሴሎም ናቸው፤ እነዚህ ሦስቱ ከከነዓናዊቱ ሴዋ የተወለዱለት ልጆች ናቸው። የይሁዳም የበኩር ልጅ ዔር በጌታ ፊት ክፉ ነበረ፤ እርሱም ገደለው።