Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 3:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ሴቲቱም ዛፉ ለመብላት ያማረ እንደሆነ፥ ለዓይንም እንደሚያስጎመጅ፥ ጥበብ ለማግኘትም የሚመኙት እንደሆነ አየች፤ ከፍሬውም ወሰደችና በላች፤ ለባልዋም ደግሞ ሰጠችው፤ እርሱም በላ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ሴቲቱ የዛፉ ፍሬ ለመብል መልካም፣ ለዐይን የሚያስደስትና ጥበብንም ለማግኘት የሚያጓጓ እንደ ሆነ ባየች ጊዜ፣ ከፍሬው ወስዳ በላች፤ ከርሷም ጋራ ለነበረው ለባሏ ሰጠችው፤ እርሱም በላ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ሴቲቱም ዛፉ የሚያምር፥ ፍሬውም ለመብላት የሚያስጐመዥና ጥበብን የሚያስገኝ እንደ ሆነ ባየች ጊዜ ከፍሬው ወስዳ በላች፤ ለባሏም ከፍሬው ሰጠችው፤ እርሱም በላ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ሴቲ​ቱም ዛፉ ለመ​ብ​ላት ያማረ እን​ደ​ሆነ፥ ለዐ​ይ​ንም ለማ​የት እን​ደ​ሚ​ያ​ስ​ጐ​መጅ፥ መል​ካ​ም​ንም እን​ደ​ሚ​ያ​ሳ​ውቅ ባየች ጊዜ፥ ከፍ​ሬው ወሰ​ደ​ችና በላች፤ ለባ​ል​ዋም ደግሞ ሰጠ​ችው፤ እር​ሱም ከእ​ር​ስዋ ጋር በላ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ሴቲቱም ዛፉ ለመብላት ያማረ እንደ ሆነ፤ ለዓይንም እንደሚያስጎመጅ፤ ለጥበብም መልካም እንድ ሆነ አየች፤ ከፍሬውም ወሰደችና በላች ለባልዋም ደግሞ ሰጠችው እርሱም ከእርስው ጋር በላ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 3:6
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ምክንያቱም በዓለም ያለው ሁሉ፥ የሥጋ ምኞት፥ የዐይን ምኞት፥ በኑሮ ደረጃ መመካት፥ ከዓለም ነው እንጂ ከአብ አይደለም።


የተታለለም አዳም አይደለም፤ ሴቲቱ ግን ተታልላ በመተላለፍ ወደቀች፤


አንድ ቀን ማታ፥ ዳዊት ከአልጋው ተነሥቶ በቤተ መንግሥቱ ሰገነት ወዲያና ወዲህ ይመላለስ ነበር፤ ከሰገነቱ ላይ እንዳለም፥ አንዲት ሴት ገላዋን ስትታጠብ አየ፤ ሴቲቱም እጅግ ውብ ነበረች።


በምርኮ መካከል አንድ ያማረ የሰናዖር ካባ፥ ሁለት መቶም ሰቅል ብር፥ ሚዛኑም ኀምሳ ሰቅል የሆነ ወርቅ አይቼ ተመኘኋቸው፥ ወሰድኋቸውም፤ እነሆም፥ በድንኳኔ ውስጥ በመሬት ተሸሽገዋል፥ ብሩም ከሁሉ በታች ነው።”


እነርሱ ግን በአዳም ቃል ኪዳንን ተላልፈዋል፤ በዚያም ቦታ እኔን አታለውኛል።


የእግዚአብሔር ልጆችም የሰውን ሴቶች ልጆች መልካሞች እንደ ሆኑ አዩ፥ ከመረጡአቸውም ሁሉ ሚስቶችን ለራሳቸው ወሰዱ።


አንተም የሰው ልጅ ሆይ፥ ምሽጋቸውን፥ የክብራቸውን ደስታ፥ የዓይናቸውን ምኞት፥ የነፍሳቸውን ናፍቆት፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን በወሰድሁባቸው ቀን፥


የሰው ልጅ ሆይ፥ እነሆ የዐይንህን ምኞት በቅፅበት እወስድብሃለሁ፤ ቢሆንም ግን ዋይታ አታሰማ፥ አታልቅስ፥ እንባህንም አታፍስስ።


እኔ ግን እላችኋለሁ፤ ወደ ሴት አይቶ የተመኛት ሁሉ ከወዲሁ በልቡ ከእርሷ ጋር አመንዝሮአል።


ለእስራኤል ቤት እንዲህ በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ የኃይላችሁ ትምክሕት፥ የዓይናችሁ ምኞት፥ የነፍሳችሁ ናፍቆት የሆነውን መቅደሴን አረክሳለሁ፤ ትታችኋቸው የሄዳችሁ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁ በሰይፍ ይወድቃሉ።


እያደርም የጌታው ሚስት ዐይኗን ጣለችበት፤ አፍ አውጥታም፥ “አብረኸኝ ተኛ” አለችው።


አዳምንም አለው፦ “የሚስትህን ቃል ሰምተሃልና፥ እንዳትበላ ካዘዝሁህ ዛፍም ከእርሱ በልተሃልና ምድር ከአንተ የተነሣ የተረገመች ትሁን፥ በሕይወት ዘመንህም ሁሉ በድካም ከእርሷ ትበላለህ፤


አዳምም፦ “ከእኔ ጋር እንድትሆን የሰጠኽኝ ሴት እርሷ ከዛፉ ሰጠችኝና በላሁ” አለ።


“ከዐይኖቼ ጋር ቃል ኪዳን ገብቻለሁ፥ እንግዲህ ቈንጆይቱን እንዴት በፍትወት እመለከታለሁ?


ሚስቱም በሰርጉ በዓል ሰባት ቀን ሙሉ እያለቀሰች ጨቀጨቀችው፤ አጥብቃ ስለ ነዘነዘችውም በመጨረሻ በሰባተኛው ቀን ነገራት፤ እርሷም በበኩሏ የእንቈቅልሹን ፍች ለሕዝቧ ነገረች።


ስለዚህ እርሱም ከእርሱ ጋር አብሮት ወደ ቤቱ ሄደ፤ ከእርሱም ጋር ዳቦ በላ፥ ውሀም ጠጣ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች