ዘፍጥረት 36:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከብታቸው ስለ በዛ በአንድነት ይቀመጡ ዘንድ አልቻሉም፥ በእንግድነት የተቀመጡባትም ምድር ከከብታቸው ብዛት የተነሣ ልትበቃቸው አልቻለችም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ብዙ ሀብት ስለ ነበራቸው ዐብረው መኖር አልቻሉም፤ የነበሩበትም ስፍራ ከከብቶቻቸው ብዛት የተነሣ ሊበቃቸው አልቻለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህንንም ያደረገበት ምክንያት እርሱና ያዕቆብ ብዙ ንብረት ስለ ነበራቸው፥ የሚሰፍሩበት ምድር ለሁለት ስላልበቃ ነው፤ ሁለቱም ብዙ እንስሶች ስለ ነበሩአቸው አብረው ለመኖር አልቻሉም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከብታቸው ስለበዛ በአንድነት ይቀመጡ ዘንድ አልቻሉም፤ በእንግድነት የተቀመጡባትም ምድር ከከብታቸው ብዛት የተነሣ ልትበቃቸው አልቻለችም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከብታቸው ስለ በዛ በአንድነት ይቀመጡ ዘንድ አልታሉም በእንግድነት የተቀመጡባትም ምድር ከከብታቸው ብዛት የተነሣ ልትበቃቸው አልቻለችም። |
በእንግድነት የምትኖርባትን ምድር፥ የከነዓን ምድር ሁሉ፥ ለዘለዓለም ግዛት ይሆንህ ዘንድ ለአንተና ከአንተ በኋላ ለዘርህ እሰጣለሁ፥ አምላክም እሆናቸዋለሁ።”
ስደተኛ ሆነህ የተቀመጥህባትን እግዚአብሔርም ለአብርሃምን የሰጣትን ምድር ትወርስ ዘንድ የአብርሃም በረከት ለአንተ ይስጥህ፥ ለዘርህም እንዲሁ።”
በምትኖሩባት ምድር ላይ ብዙ ዘመን እንድትኖሩ፥ በዕድሜአችሁ ሙሉ በድንኳን ውስጥ ተቀመጡ እንጂ ቤትን አትሥሩ፥ ዘርንም አትዝሩ፥ ወይንን አትትከሉ ወይም የወይን ቦታ አይኑራችሁ።’
ለባዕድ አገር እያለም በተስፋ ቃል በተሰጠው ምድር፥ ያን የተስፋ ቃል አብረውት ወራሾች እንደሆኑት እንደ ይስሐቅና እንደ ያዕቆብ በእምነት በድንኳን ኖረ፤