Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 36:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ዔሳውም በሴይር ተራራ ተቀመጠ፥ ዔሳው ኤዶም ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ስለዚህ ኤዶም የተባለው ዔሳው መኖሪያውን በተራራማው አገር በሴይር አደረገ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ስለዚህ ኤዶም የተባለው ዔሳው በተራራማው አገር በኤዶም ተቀመጠ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ዔሳ​ውም በሴ​ይር ተራራ ተቀ​መጠ፤ ዔሳ​ውም ኤዶም ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ዔሳውም በሴይር ተራራ ተቀመጠ ዔሳውም ኤዶም ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 36:8
21 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከዚህ በኋላ ያዕቆብ ወደ ወንድሙ ወደ ዔሳው ወደ ሴይር ምድር ወደ ኤዶም አገር ከፊቱ መልእክተኞችን ላከ፥


ዔሳውን ግን ጠላሁት፤ ተራራውን አጠፋሁ፥ ርስቱንም ለምድረ በዳ ቀበሮች ሰጠኋቸው።


የአሞንና የሞዓብም ልጆችም በሴይርም ተራራ በሚኖሩት ላይ ፈጽመው ሊገድሉአቸውና ሊያጠፉአቸውም ተነሥተውባቸው ነበር፤ በሴይርም የሚኖሩትን ካጠፉ በኋላ አንዱ ሌላውን በማገዝ እርስ በርስ ተጠፋፉ።


እንግዲህ አሁን፥ እነሆ፥ እስራኤል ከግብጽ ምድር በወጡ ጊዜ እንዳይወርሯቸው ያልፈቀድህላቸው፥ ነገር ግን ትተዋቸው ያላጠፉአቸው፥ የአሞንና የሞዓብ ልጆች የሴይርም ተራራ ሰዎች፥


የስምዖንም ልጆች አምስት መቶ ሰዎች ወደ ሴይር ተራራ ሄዱ፤ አለቆቻቸውም የይሽዒ ልጆች፥ ፈላጥያ፥ ነዓርያ፥ ረፋያ፥ ዑዝኤል ነበሩ።


ለይስሐቅም ያዕቆብንና ዔሳውን ሰጠሁት፤ ለዔሳውም የሴይርን ተራራ ርስት አድርጌ ሰጠሁት፤ ያዕቆብም ልጆቹም ወደ ግብጽ ወረዱ።


የሴይርን ተራራ ለዔሳው ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ እኔ ከምድራቸው የጫማ መርገጫ ታህል እንኳ አልሰጣችሁምና አትጣሉአቸው።


የዔሳው ትውልድ ይህ ነው፥ እርሱም ኤዶም ነው።


የሖር ሰዎችንም በሴይር ተራራቸው በበረሀ አጠገብ እስካለች እስከ ኤል ፋራን ድረስ መቱ።


በሴይር ተራራ የሚኖሩ የኤዶማውያን አባት የዔሳው ትውልድም ይህ ነው።


ሕዝቡንም እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፦ በሴይር ላይ በተቀመጡት በወንድሞቻችሁ በዔሳው ልጆች አገር ታልፋላችሁ፥ እነርሱም ይፈሩአችኋል፤ እንግዲህ እጅግ ተጠንቀቁ።


ሖራውያንን ከፊታቸው አጥፍቶ፥ በሴይር ለተቀመጡት ለዔሳው ልጆች እንዳደረገ፥ እንዲሁ ለእነርሱ አደረገ፥ እነርሱንም ቀምተው በስፍራቸው እስከ ዛሬ ድረስ ተቀመጡ።


እንዲሁም ደግሞ በሞዓብም፥ በአሞንም ልጆች መካከል፥ በኤዶምያስም በምድሪቱም ሁሉ ላይ የነበሩ አይሁድ ሁሉ፥ የባቢሎን ንጉሥ በይሁዳ ትሩፍ እንዳስቀረ፥ የሳፋንንም ልጅ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በላያቸው እንደ ሾመው በሰሙ ጊዜ፥


ዔሳውም ያዕቆብን፥ “ከዚህ ከቀዩ ወጥ አብላኝ፥ እኔ እጅግ እርቦኛልና!” አለው፤ (ኤዶም የተባለውም በዚህ ምክንያት ነበር።)


እንዲህም ብሎ አዘዛቸው፦ “ለጌታዬ ለዔሳው፥ አገልጋይህ ያዕቆብ እንዲህ ይላል፥ ‘በላባ ዘንድ በስደት ተቀመጥሁ፥ እስከ አሁን ድረስ ቆየሁ፥’” ብላችሁ ንገሩት


ማግዲኤል አለቃ፥ ዒራም አለቃ፤ እነዚህ በግዛታቸው ምድር በየመኖሪያቸው የኤዶም አለቆች ናቸው። የኤዶማውያን አባት ዔሳው ነው።


ሳኦል በእስራኤል ላይ ከነገሠ በኋላ፥ በዙሪያው ያሉትን ጠላቶቹን ሞዓብን፥ አሞናውያንን፥ ኤዶምን፥ የጾባን ነገሥታትና ፍልስጥኤማውያንን ወጋቸው። በተዋጋበት ስፍራ ሁሉ ድል አድራጊ ነበር።


የአብድዩ ራእይ። ጌታ አምላክ ስለ ኤዶምያስ እንዲህ ይላል፦ ከጌታ መልእክት ሰምተናል፥ መልእክተኛ ወደ አሕዛብ ተልኮ፦ ተነሡ፥ በላይዋም በጦርነት እንነሣ ብሏል።


በተሰነጠቀ ዓለት ውስጥ የምትኖር፥ ማደሪያህንም ከፍ ከፍ ያደረግህ፥ በልብህም፦ ወደ ምድር የሚያወርደኝ ማን ነው? የምትል አንተ ሆይ፥ የልብህ ትዕቢት አታልሎሃል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች