ዘፍጥረት 34:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሐሞርም እንዲህ ብሎ ነገራቸው፥ “ልጄ ሴኬም በልጃችሁ ፍቅር ነፍሱ ተወስዳለችና ሚስት እንድትሆነው እባካችሁ እርሷን ስጡት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኤሞር ግን እንዲህ አላቸው፤ “ልጄ ሴኬም ልቡ በልጃችሁ ፍቅር ተነድፏል፤ እባካችሁ እንዲያገባት ፍቀዱለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሐሞር ግን እንዲህ አላቸው፤ “ልጄ ሴኬም ልጃችሁን በጣም ወዶአታል፤ ስለዚህ እንዲያገባት ፍቀዱለት፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤሞርም እንዲህ ብሎ ነገራቸው፥ “ልጄ ሴኬም ልጃችሁን ወዶአታልና ሚስት እንድትሆነው እርስዋን ስጡት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኤሞርም እንዲህ ብሎ ነገራቸው፦ ልጄ ሴኬም በልጃችሁ ፍቅር ልቡ ተነድፎአልና ሚስት እንድትሆነው እባካችሁ እርስዋን ስጡት። |
የያዕቆብም ልጆች ይህንን በሰሙ ጊዜ ከመስክ መጡ፥ የያዕቆብን ልጅ በመተኛቱ በእስራኤል ላይ ኀፍረትን ስላደረገ አዘኑ፥ እንዲህ አይደረግምና እጅግም ተቈጡ።
ጌታ ለእስራኤላውያን፥ “አሕዛብ ሴቶችን ያገባችሁ እንደሆነ በእርግጥ ወደ አማልእክታቸው ስለሚስቡአችሁ እነርሱን አታግቡ” ብሎ አስጠንቅቆአቸው ነበር፤ እነዚህን ሰሎሞን የወደዳቸው ሴቶች ጌታ እንዳይጋቡ ከከለከላቸው ሕዝቦች መካከል ናቸው፤ ሰሎሞን ግን ከእነርሱ ጋር በፍቅር ተሰባበረ።