ነገራቸውም በኤሞር ልጅ በሴኬምና በኤሞር ዘንድ የተወደደ ሆነ።
ያቀረቡትም ሐሳብ ለኤሞርና ለልጁ ለሴኬም መልካም መስሎ ታያቸው።
ይህም አባባል ለሐሞርና ለልጁ ለሴኬም መልካም መስሎ ታያቸው፤
ነገራቸውም ኤሞርንና የኤሞርን ልጅ ሴኬምን ደስ አሰኛቸው።
ነገራቸውም በኤሞር ልጅ በሴኬምን በኤሞር ዘንድ የተወደደ ሆነ።
ትገረዙ ዘንድ እኛን ባትሰሙ ግን ልጃችንን ይዘን እንሄዳለን።”
ወጣቱም ልጅ፥ የያዕቆብን ልጅ ወድዶአልና፥ ያሉትን ያደርግ ዘንድ አልዘገየም። እርሱም በአባቱ ቤት ካሉት ሁሉ የከበረ ነበረ።
በፈርዖንም ቤት፥ “የዮሴፍ ወንድሞች መጡ ተብሎ ወሬ ተሰማ፥” በሰሙትም ነገር ፈርዖንና አገልጋዮቹ ደስ ተሰኙበት።