ያዕቆብም መንገዱን ሄደ፥ የእግዚአብሔር መላእክትም አጋጠሙት።
ያዕቆብም ጕዞውን ቀጠለ፤ የእግዚአብሔርም መላእክት ተገናኙት፤
ያዕቆብ በጒዞ ላይ ሳለ የእግዚአብሔር መላእክት በመንገድ ተገናኙት።
ያዕቆብም መንገዱን ሄደ፤ በዐይኖቹም የእግዚአብሔርን ሠራዊት ከትመው አየ፤ የእግዚአብሔር መላእክትም ተገናኙት።
ያዕቆብም መንገዱን ሄደ የእግዚአብሔር መላእክትም ተገናኙት።
እግዚአብሔርም ከአብርሃም ጋር ንግግሩን በጨረሰ ጊዜ ሄደ፥ አብርሃምም ወደ ስፍራው ተመለሰ።
ርብቃንም መረቁአትና፦ “አንቺ እኅታችን፥ እልፍ አእላፋት ሁኚ፥ ዘርሽም የጠላቶችን ደጅ ይውረስ” አሉአት።
ወንዶቹንና ሴቶቹን ልጆቼን እንድስም ስለምን አልፈቀድህልኝም? ይህንም በስንፍና አደረግህ።
ይህ ችግረኛ ጮኸ፥ ጌታም ሰማው፥ ከመከራውም ሁሉ አዳነው።
በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋልና፥
ጳውሎስ ቢሆን አጵሎስም ቢሆን ኬፋም ቢሆን ዓለምም ቢሆን ሕይወትም ቢሆን ሞትም ቢሆን ያለውም ቢሆን የሚመጣውም ቢሆን፥ ሁሉ የእናንተ ነው፤
በዚህም ብዙ ልዩ ልዩ የእግዚአብሔር ጥበብ አሁን በቤተ ክርስቲያን በኩል በሰማያዊ ስፍራ ውስጥ ላሉት አለቆችና ሥልጣናት እንድትታወቅ ነው።
ከመላእክት ይልቅ እጅግ የላቀ ስምን በተቀበለ መጠን፥ እንደዚሁ ከእነርሱ እጅግ ልቆ ይበልጣል።