ዔሳውም አባቱ ስለ ባረከው በያዕቆብ ቂም ያዘበት፥ ዔሳውም በልቡ አለ፦ “ለአባቴ የልቅሶ ቀን ቀርቦአል፥ ከዚያም በኋላ ወንድሜን ያዕቆብን እገድለዋለሁ።”
ዘፍጥረት 27:42 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለርብቃም ይህ የታላቁ ልጇ የዔሳው ቃል ደረሰላት፥ ታናሹን ልጇን ያዕቆብንም አስጠርታ አስመጣችው፥ አለችውም፦ “እነሆ፥ ወንድምህ ዔሳው ሊገድልህ ይፈቅዳል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ርብቃ፣ ታላቁ ልጇ ዔሳው ያሰበው በተነገራት ጊዜ ታናሹን ልጇን ያዕቆብን አስጠርታ እንዲህ አለችው፤ “ወንድምህ ዔሳው ሊገድልህ ጊዜ እየጠበቀ ነው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ርብቃ የዔሳውን ዕቅድ ስለ ሰማች፥ ያዕቆብን ጠርታ እንዲህ አለችው፤ “አድምጠኝ፤ ወንድምህ ዔሳው አንተን በመግደል ሊበቀልህ አስቦአል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለርብቃም ታላቁ ልጅዋ ዔሳው ያለው ተነገራት፤ ታናሹን ልጅዋን ያዕቆብንም ልካ ጠራችው፤ አለችውም፥ “እነሆ ወንድምህ ዔሳው ያድድንሃል፤ ሊገድልህም ይፈልጋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለርብቃም ይህ የታላቁ ልጅዋ የዔሳው ቃል ደረሰላት፤ ታናሹን ልጅዋን ያዕቆብንም አስጠርታ አስመጣችው አለችውም፦ እነሆ ወንድምህ ዔሳ ሊገድልህ ይፈቅዳል። |
ዔሳውም አባቱ ስለ ባረከው በያዕቆብ ቂም ያዘበት፥ ዔሳውም በልቡ አለ፦ “ለአባቴ የልቅሶ ቀን ቀርቦአል፥ ከዚያም በኋላ ወንድሜን ያዕቆብን እገድለዋለሁ።”