ዘፍጥረት 21:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁንም በእኔም በልጄም በልጅ ልጄም ክፉ እንዳታደርግብኝ በእግዚአብሔር ማልልኝ፥ ነገር ግን ለአንተ ቸርነትን እንዳደረግሁ አንተም ለእኔ ለተቀመጥህባትም ምድር ቸርነትን ታደርጋለህ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ እኔንና ልጆቼን፣ ዘሬንም በመሸንገል አንዳች ክፉ ነገር እንዳታደርስብን በእግዚአብሔር ፊት ማልልኝ። እኔ ለአንተ ቸርነት እንዳደረግሁ፣ አንተም ለእኔና በእንግድነት ለተቀመጥህባት ለዚህች ምድር ቸርነት አድርግ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔንም ሆነ ልጆቼን ወይም ዘሮቼን በማታለል እንዳትበድል እዚህ በእግዚአብሔር ስም ማልልኝ፤ እኔ ለአንተ ታማኝነትን አሳይቻለሁ፤ አንተም ለእኔና ለዚህች በመጻተኛነት ለምትኖርባት አገር ታማኝነትን እንደምታሳይ ማልልኝ” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም በእኔም፥ በልጄም፥ በወገኔም፥ ከእኔም ጋር ባለ ክፉ እንዳታደርግብኝ በእግዚአብሔር ማልልኝ፤ ነገር ግን በእንግድነት መጥተህ ለአንተ ቸርነት እንዳደረግሁ አንተም ለእኔ፥ ለተቀምጥህባትም ምድር ቸርነትን ታደርጋለህ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁንም በእኔም በልጄም በልጅ ልጄም ክፉ እንዳታደርግብኝ በእግዚአብሔር ማልልኝ፤ ነገር ግን ለአንተ ቸርነትን እንዳደረግሁ አንተም ለእኔ ለተቀመጥህባትም ምድር ቸርነትን ታደርጋለህ። |
“እጅህን ከጭኔ በታች አድርግ፥ እኔም አብሬ ከምኖራቸው ከከነዓን ሴቶች ልጆች ለልጄ ሚስት እንዳትወስድለት በሰማይና በምድር አምላክ በእግዚአብሔር አምልሃለሁ፥
ነገር ግን አባቴ ክፉ አስቦብህ፥ ይህን ሳላሳውቅህ ብቀርና በሰላም እንድትሄድ ባላደርግ፥ ጌታ ክፉ ያድርግብኝ፤ ከዚያም የባሰ ያምጣብኝ። ጌታ ከአባቴ ጋር እንደ ነበር እንደዚሁ ከአንተም ጋር ይሁን።
ዮናታንም ዳዊትን፤ “ ‘በአንተና በእኔ፥ በዘሮችህና በዘሮቼ መካከል ጌታ ለዘለዓለም ምስክር ነው’ ተባብለን ወዳጅነታችን እንዲጸና በጌታ ስም ስለ ተማማልን እንግዲህ በሰላም ሂድ” አለው። ከዚያም ዳዊት ተነሥቶ ሄደ፤ ዮናታንም ወደ ከተማ ተመለሰ።
ዳዊትም፥ “ታዲያ ወራሪው ሠራዊት ወዳለበት መርተህ ትወስደኛለህን?” ሲል ጠየቀው። እርሱም፥ “እንደማትገድለኝ ወይም ለጌታዬ አሳልፈህ እንደማትሰጠኝ በእግዚአብሔር ማልልኝ እንጂ እነዚህ ወራሪዎች ወዳሉበት አደርስሃለሁ” አለው።