ዘፍጥረት 16:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም የሜዳ አህያን የሚመስል ሰው ይሆናል፥ እጁ በሁሉ ላይ ይሆናል፥ የሁሉም እጅ ደግሞ በእርሱ ላይ ይሆናል፥ እርሱም በወንድሞቹ ሁሉ ፊት ይኖራል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም እንደ ዱር አህያ ይሆናል፤ እጁንም ባገኘው ሰው ሁሉ ላይ ያነሣል፤ ያገኘውም ሁሉ እጁን ያነሣበታል፤ ከወንድሞቹ ሁሉ ጋራ እንደ ተጣላ ይኖራል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን እንደ ሜዳ አህያ ይሆናል፤ ሰውን ሁሉ ይቃወማል፤ ሰዎችም እርሱን ይቃወሙታል፤ ዘመዶቹን በመጥላት ተለይቶ ይኖራል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም የበረሃ ሰው ይሆናል፤ እጁ በሁሉ ላይ ይሆናል፤ የሁሉም እጅ ደግሞ በእርሱ ላይ ይሆናል፤ እርሱም በወንድሞቹ ሁሉ ፊት ይኖራል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም የበዳ አህያን የሚመስል ሰው ይሆናል፤ እጁ በሁሉ ላይ ይሆናል፥ የሁሉም እጅ ደግሞ በእርሱ ላይ ይሆናል፤ እርሱም በወንድሞቹ ሁሉ ፊት ይኖራል። |
ዘሮቹም ከግብጽ በስተ ምሥራቅ ወደ አሦር በምትወስደው መንገድ በሐዊላና በሹር መካከል ሲሰፍሩ፤ የኖረውም በወንድሞቹ ሁሉ ፊት በተቃርኖ ነበር።
ምግብ ሊበሉ ተቀመጡ፥ ዓይናቸውንም አንሥተው ሲያዩ፥ እነሆ የእስማኤላውያን ነጋዴዎች ወደ ግብጽ ለመውረድ ከገለዓድ ይመጣሉ፥ ግመሎቻቸውም ሽቱና በለሳን፥ ከርቤም ተጭነው ነበር።