ዘፍጥረት 15:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሞራዎችም በሥጋው ላይ ወረዱ፥ አብራምም አበረራቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሞሮችም ሥጋውን ለመብላት ወረዱ፤ አብራም ግን አባረራቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሞራዎች የተቈራረጠውን ሥጋ ለመብላት ሲመጡ አብራም አባረራቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሞራዎችም በተቈረጠው ሥጋቸው ላይ ወረዱ፤ አብራምም በእነርሱ ዘንድ ተቀምጦ አባረራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሞራዎችም በሥጋው ላይ ወረዱ፥ አብራምም አበረራቸው። |
እንዲህም በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ትልቅ ክንፎች፥ ረጅም ማርገብገቢያ ያለው፥ ዝንጉርጉርና ብዙ ላባ ያለው ትልቅ ንስር ወደ ሊባኖስ መጣ፥ የዝግባንም ጫፍ ወሰደ።
ትልልቅ ክንፎችና ብዙ ላባ ያለው ሌላ አንድ ትልቅ ንስር ነበረ፥ እነሆም ይህ ወይን እንዲያጠጣው ሥሩን ወደ እርሱ አዘነበለ፥ ቅርንጫፉንም ከተተከለበት ከመደብ ወደ እርሱ ሰደደ።