ሎጥም ዓይኑን አነሣ፥ በዮርዳኖስ ዙሪያ ያለውንም አገር ሁሉ ውኃ የሞላበት መሆኑን አየ፥ እግዚአብሔር ሰዶምንና ገሞራን ከማጥፋቱ አስቀድሞ እስከ ጾዓር ድረስ እንደ ጌታ ገነት በግብጽ ምድር አምሳል ነበረ።
ዘፍጥረት 13:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምድር ሁሉ በፊትህ አይደለችምን? ከእኔ ትለይ ዘንድ እለምንሃለሁ፥ አንተ ግራውን ብትወስድ እኔ ወደ ቀኝ እሄዳለሁ፥ አንተም ቀኙን ብትወስድ እኔ ወደ ግራ እሄዳለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይኸው እንደምታየው አገሩ ሰፊ ነው፤ ብንለያይ ይሻላል። አንተ ግራውን ብትመርጥ፣ እኔ ወደ ቀኝ እሄዳለሁ፤ አንተ ቀኙን ብትመርጥ፣ እኔ ወደ ግራ አመራለሁ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምድሪቱ ሁሉ በፊትህ አይደለችምን? ከእኔ ተለይተህ ሂድ፤ አንተ ወደ ግራ ብትሄድ እኔ ወደ ቀኝ እሄዳለሁ፤ ወይም አንተ ወደ ቀኝ ብትሄድ እኔ ወደ ግራ እሄዳለሁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ፥ ምድር ሁሉ በፊትህ አይደለችምን? ከእኔ ትለይ ዘንድ እለምንሃለሁ፤ አንተ ወደ ግራው ብትሄድ እኔ ወደ ቀኝ እሄዳለሁ፤ አንተም ወደ ቀኙ ብትሄድ እኔ ወደ ግራ እሄዳለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምድር ሁሉ በፊትህ አይደለችምን? ከእኔ ትለይ ዘንድ እለምንሃለሁ አንተ ግራውን ብትወስድ እኔ ወደ ቀኝ እሄዳለሁ፤ አንተም ቀኙን ብትወስድ እኔ ወደ ግራ እሄዳለሁ። |
ሎጥም ዓይኑን አነሣ፥ በዮርዳኖስ ዙሪያ ያለውንም አገር ሁሉ ውኃ የሞላበት መሆኑን አየ፥ እግዚአብሔር ሰዶምንና ገሞራን ከማጥፋቱ አስቀድሞ እስከ ጾዓር ድረስ እንደ ጌታ ገነት በግብጽ ምድር አምሳል ነበረ።
አሁን ደግሞ፥ እነሆ፥ በእጅህ ካለው ሰንሰለት ዛሬ ፈታሁህ። ከእኔ ጋር ወደ ባቢሎን መምጣት መልካም መስሎ ቢታይህ፥ ና፥ እኔም በበጎ ዐይን እመለከትሀለው፤ ከእኔ ጋር ወደ ባቢሎን መምጣት መልካም መስሎ ባይታይህ ግን፥ ቅር፤ እነሆ ተመልከት፥ አገሪቱ ሁሉ በፊትህ ናት፤ ለመሄድ መልካም መስሎ ወደሚታይህ ትክክልም ነው ብለህ ወደምታስበው ስፍራ ወደዚያ ሂድ።
እንግዲህ ፈጽሞ የእርስ በእርስ ሙግት በመካከላችሁ መፍጠር ለእናንተ ሽንፈት ነው። ይልቅስ ብትበደሉ አይሻልምን? እንዲሁም ብትታለሉ አይሻልምን?