ዘፍጥረት 10:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኩሽም ናምሩድን ወለደ፥ እርሱም በምድር ላይ ቀዳሚው ኃያል ጦረኛ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኵሽ የናምሩድን አባት ነበረ፤ እርሱም በምድር ላይ የመጀመሪያው ኀያል ጦረኛ ሆነ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኩሽ በዓለም ላይ የመጀመሪያው ታላቅ ጦረኛ የነበረውን ናምሩድን ወለደ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኩሽም ናምሩድን ወለደ፤ እርሱም በምድር ላይ ኀያል መሆን ጀመረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኩሽም ናምሩድን ወለደ እርሱም በምድር ላይ ኃያክክ መሆንን ጀመረ። |
መልእክተኞችን በባሕር ላይ፥ የደንገል መርከቦችንም በውኃ ላይ ለምትልክ ምድር ወዮላት! እናንተ ፈጣን መልእክተኞች ሆይ፥ ወደ ረጅምና ወደ ለስላሳ ሕዝብ፥ ከቅርብም ከሩቅም አስፈሪ ወደ ሆነ ሕዝብ፥ ኀያል ወደሆነና ወደሚገዛ፥ ወንዞችም ምድራቸውን ወደሚከፍሉት ሕዝብ ሂዱ።
የያዕቆብ ትሩፍ በብዙ ሕዝቦች መካከል ከጌታ ዘንድ እንደሚመጣ ጠል፥ በሣር ላይ እንደሚወርድ ካፊያ፥ ሰውን እንደማይጠብቅ፥ የሰውን ልጆች በመጠበቅ እንደማይዘገይ ይሆናል።