ገላትያ 1:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ እንጂ ከሰው አልተቀበልሁትም ወይም አልተማርሁትም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከማንም ሰው አልተቀበልሁትም፤ ከማንም አልተማርሁትም፤ ይልቁንስ በመገለጥ ከኢየሱስ ክርስቶስ ተቀበልሁት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህን ወንጌል ኢየሱስ ክርስቶስ ገለጠልኝ እንጂ ከማንም ሰው አልተቀበልኩትም፤ ወይም ማንም ሰው አላስተማረኝም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ገለጠልኝ እንጂ፥ እኔ ከሰው አልተቀበልሁትም፤ አልተማርሁትምም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስ ክርስቶስ ገልጦልኛል እንጂ እኔ ከሰው አልተቀበልሁትም አልተማርሁትምም። |
እንደ ተገለጠልኝም ወጣሁ፤ ምናልባትም በከንቱ እንዳልሮጥ ወይም ሮጬ እንዳልሆን፥ በአሕዛብ መካከል የምሰብከውን ወንጌል፥ በመሪነታቸው ለታወቁት ለብቻቸው አስታወቅኋቸው።