ዘፀአት 4:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም “ወደ መሬት ጣለው” አለው፤ እርሱም ወደ መሬት ጣለው፥ እባብም ሆነ፤ ሙሴም ከእርሱ ሸሸ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም፣ “መሬት ላይ ጣላት” አለው። ሙሴ በትሩን መሬት ላይ ጣላት፤ እባብም ሆነች፤ ከአጠገቧም ሸሸ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም “ወደ መሬት ጣለው” አለው፤ ሙሴም ወደ መሬት በጣለው ጊዜ በትሩ ተለውጦ እባብ ሆነ፤ ሙሴም ከእርሱ ሸሸ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ወደ መሬት ጣለው” አለው፤ እርሱም በመሬት ጣለው፤ እባብም ሆነ፤ ሙሴም ከእርሱ ሸሸ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) “ወደ መሬት ጣላት፤” አለው፤ እርሱም በመሬት ጣላት፤ እባብም ሆነች፤ ሙሴም ከእርሷ ሸሸ። |
“ፈርዖን ‘ተአምራትን በማድረግ ማንነታችሁን አሳዩኝ’ ሲላችሁ፥ አሮንን ‘በትርህን ወስደህ እባብ እንዲሆን በፈርዖን ፊት ጣለው’ በለው፥ በትሩም እባብ ይሆናል።”