ዘፀአት 39:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ሙሴን እንዳዘዘው በመጠምጠሚያው ላይ እንዲያንጠለጥሉት ሰማያዊ ፈትል አሰሩበት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ከመጠምጠሚያው ጋራ ለማያያዝ ሰማያዊ ፈትል አሰሩበት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱንም እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ከመጠምጠሚያው ፊት በሰማያዊ ክር አሰሩት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው፥ በአክሊሉ ላይ ያንጠለጥሉት ዘንድ ሰማያዊውን ፈትል አሰሩበት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመጠምጠሚያውም ላይ ያንጠለጥሉት ዘንድ ሰማያዊውን ፈትል አሰሩበት። |
የሚሠሩአቸውም ልብሶች እነዚህ ናቸው፤ የደረት ኪስ፥ ኤፉድ፥ ቀሚስ፥ የተጠለፈ እጀ ጠባብ፥ መጠምጠሚያና መታጠቂያ፤ ካህን እንዲሆንልኝ ለወንድምህ ለአሮንና ለልጆቹ የተቀደሰ ልብስ ይሥሩላቸው።