ዘፀአት 38:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሺህ ሰባት መቶ ሰባ አምስት ሰቅል የምሰሶዎቹን ኩላቦችና ዘንጎች ሠራ፥ የምሰሶዎቹንም ጉልላቶች ለበጠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንድ ሺሕ ሰባት መቶ ሰባ ዐምስት ሰቅሎችን ለምሰሶዎቹ ኵላቦች፣ የምሰሶዎቹን ዐናት ለመለበጥና ዘንጎቻቸውንም ለመሥራት አገልግሎት ላይ ውለው ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በቀረውም ሠላሳ ኪሎ ብር ባጽልኤል ለምሰሶዎቹ ዘንጎችን፥ ኩላቦችንና ጒልላቶችን ሠራ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሺህ ሰባት መቶ ሰባ አምስት ሰቅል የምሰሶዎቹን ኵላቦችና ዘንጎች አደረገ፤ የምሰሶዎቹንም ጕልላቶች ለበጠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሺህ ሰባት መቶ ሰባ አምስት ሰቅል የምሰሶቹን ኩላቦችና ዘንጎች አደረገ፥ የምሰሶቹንም ጉልላቶች ለበጠ። |
መቶው የብር መክሊት የመቅደሱንና የመጋረጃውን እግሮች ለመሥራት ነበረ፤ ከመቶ መክሊት መቶ እግሮች ተሠሩ ይኸውም ለአንድ እግር አንድ መክሊት ማለት ነው።