ዘፀአት 16:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጥዋት ጥዋት እያንዳንዱ የሚበላውን ያህል ሰበሰበ፤ ፀሐይም በሞቀ ጊዜ ቀለጠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በየማለዳው እያንዳንዱ የሚያስፈልገውን ያህል ሰበሰበ፤ ፀሓዩ እየበረታ በሄደም ጊዜ ቀለጠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በየማለዳው እያንዳንዱ የሚበቃውን ያኽል ይሰበስብ ነበር፤ ፀሐይ ከሞቀ በኋላ ግን በመሬት ላይ የቀረው ሁሉ ይቀልጥ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰውም ሁሉ ለየራሱ ጥዋት ጥዋት ሰበሰበ፤ ፀሐይም በተኰሰ ጊዜ ቀለጠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰውም ሁሉ ዕለት ዕለት የሚበላውን ያህል በጥዋት ለቀመ፤ ፀሐይም በተኮሰ ጊዜ ቀለጠ። |
እንዲህም ሆነ በስድስተኛው ቀን ሁለት እጥፍ አድርገው ሁለት ዖሜር ምግብ ለአንድ ሰው ሰበሰቡ፤ የማኅበሩም መሪዎች ሁሉ መጥተው ለሙሴ ነገሩት።
ኢየሱስም “ገና ጥቂት ጊዜ ብርሃን ከእናንተ ጋር ነው። ጨለማ እንዳይደርስባችሁ ብርሃን ሳለላችሁ ተመላለሱ፤ በጨለማም የሚመላለስ ወዴት እንዲሄድ አያውቅም።
እርሱ፥ “በተወደደ ሰዓት ሰማሁህ፤ በመዳንም ቀን ረዳሁህ፤” ይላልና፤ እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ እነሆ፥ የመዳንም ቀን አሁን ነው።