ዘዳግም 4:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ትወርሱአት ዘንድ ተሻግራችሁ በምትገቡባት ምድር የምታደርጉትን ሥርዓትና ሕግጋት እንዳስተምራችሁ ጌታ በዚያን ጊዜ አዘዘኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ በምትወርሷት ምድር ውስጥ የምትከተሏቸውን ሥርዐትና ሕግ እንዳስተምራችሁ በዚያ ጊዜ እግዚአብሔር አዘዘኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔም፥ ድል አድርጋችሁ በምትወርሱአት ምድር ስትኖሩ ልትፈጽሙት የሚገባውን ሕግና ሥርዓት ሁሉ እንዳስተምራችሁ እግዚአብሔር አዞኛል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ትወርሱአት ዘንድ ተሻግራችሁ በምትገቡባት ምድር የምታደርጉአትን ሥርዐትና ፍርድ አስተምራችሁ ዘንድ እግዚአብሔር በዚያን ጊዜ አዘዘኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ትወርሱአት ዘንድ ተሻግራችሁ በምትገቡባት ምድር የምታደርጉአትን ሥርዓትና ፍርድ አስተምራችሁ ዘንድ እግዚአብሔር በዚያን ጊዜ አዘዘኝ። |