ዘዳግም 3:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ጌታ አምላካችን ደግሞ የባሳንን ንጉሥ ዖግን ሕዝቡንም ሁሉ በእጃችን አሳልፎ ሰጠን፥ እኛም አንድ ሰው እንኳ ሳናስቀርለት አጠፋነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ አምላካችን እግዚአብሔር የባሳንን ንጉሥ ዐግን ከመላው ሰራዊቱ ጋራ ሁሉ እንደዚሁ በእጃችን ላይ ጣላቸው፤ እኛም አንድ እንኳ በሕይወት ሳናስቀር አጠፋናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ስለዚህም እግዚአብሔር አምላካችን የባሳንን ንጉሥ ዖግንና ሕዝቡን በእጃችን አሳልፎ ሰጠን፤ እኛም ከእነርሱ አንድ እንኳ ሳናስቀር ሁሉንም አጠፋን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላካችን እግዚአብሔርም ደግሞ የባሳንን ንጉሥ ዐግን ሕዝቡንም ሁሉ በእጃችን አሳልፎ ሰጠን፤ እኛም አጠፋነው፤ አንድ ሰው እንኳን ለዘር አልቀረለትም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላካችን እግዚአብሔርም ደግሞ የባሳንን ንጉሥ ዐግን ሕዝቡንም ሁሉ በእጃችን አሳልፎ ሰጠን፤ እኛም መታነው፤ አንድ ሰው እንኳ አምልጦ አልቀረለትም። |
ቂጣ አልበላችሁም፤ የወይን ጠጅ ወይም ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አልጠጣችሁም፤ ይህን ያደረግሁት እኔ እግዚአብሔር ጌታ እንደሆንኩ እንድታውቁ ነው።
ጌታም፦ ‘እርሱንና ሕዝቡን ሁሉ ምድሩንም በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼአለሁና አትፍራው፥ በሐሴቦን ይኖር በነበረው በአሞራውያን ንጉሥ በሲሖን ላይ እንዳደረግህ በእርሱም ታደርግበታለህ’ አለኝ።”
ያን ጊዜም ከተሞቹ ሁሉ ያዝን፥ የአርጎብን ግዛቶች ሁሉ፥ ከሥልሳ ከተሞች ጋር፥ በባሳን ያለውን የዖግን መንግሥት፥ ያልወሰድነው ምንም ከተማ አልነበረም።
በባሳን የነበረውን በአስታሮትና በኤድራይ የነገሠውን የዐግን መንግሥት ሁሉ፤ እርሱም ብቻ ከራፋይም የቀረ ነበረ፤ እነዚህንም ሙሴ ድል አድርጎ አስወጣቸው።