በመቃብርም መካከል የሚቀመጡ፥ ምሽቱንም በስውርም ስፍራ የሚያሳልፉ፥ የእሪያ ሥጋም የሚበሉ ናቸው። ማሰሮዎቻቸው በረከሰ ነገር የተሞሉ ናቸው።
ዘዳግም 14:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዐሣማም፥ ምንም እንኳ ሰኰናው የተሰነጠቀ ቢሆንም ስለማያመሰኩህ፥ እርሱ ለእናንተ ንጹሕ አይደለም፤ የእነዚህን ሥጋ አትብሉ፤ ጥምባቸውንም አትንኩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዐሣማም እንደዚሁ ርኩስ ነው፤ ምንም እንኳ ሰኰናው የተሰነጠቀ ቢሆንም፣ ስለማያመሰኳ፣ እርሱ ለእናንተ ንጹሕ አይደለም፤ የእነዚህን ሥጋ አትብሉ፤ ጥንባቸውንም አትንኩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዐሣማዎችን አትብሉ፤ እነርሱ ሰኮናቸው የተከፈለ ቢሆንም ስለማያመሰኩ የረከሱ ሆነው ይቈጠራሉ፤ እንደነዚህ ያሉትን እንስሶች መብላት ይቅርና በድናቸውን እንኳ አትንኩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርያም፥ ሰኰናው ስለተሰነጠቀ፥ ጥፍሩም ከሁለት ስለተከፈለ፥ ነገር ግን ሰለማያመሰኳ፥ እርሱ ለእናንተ ርኩስ ነው፤ ሥጋዉን አትብሉ፤ በድኑንም አትንኩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርያም ሰኮናው ስለ ተሰነጠቀ ነገር ግን ስላላመሰኳ፥ እርሱ ለእናንተ ርኩስ ነው፤ ሥጋውን አትብሉ፥ በድኑንም አትንኩ። |
በመቃብርም መካከል የሚቀመጡ፥ ምሽቱንም በስውርም ስፍራ የሚያሳልፉ፥ የእሪያ ሥጋም የሚበሉ ናቸው። ማሰሮዎቻቸው በረከሰ ነገር የተሞሉ ናቸው።
በመሀከላቸው ያለውን አንዱን ተከትለው ወደ መናፈሻ ስፍራው ለመግባት ሰውነታቸውን የሚቀድሱና የሚያነጹ፥ የእሪያንም ሥጋ፥ አስጸያፊ ነገርንም፥ አይጥንም የሚበሉ በአንድነት ይጠፋሉ፥ ይላል ጌታ።
በሬን የሚያርድልኝ ሰውን እንደሚገድል ነው፤ ጠቦትንም የሚሠዋ የውሻውን አንገት እንደሚሰብር ነው፤ የእህልን ቁርባን የሚያቀርብ የእርያን ደም እንደሚያቀርብ ነው። እጣንን የሚያጥን ጣዖትን እንደሚባርክ ነው። እነዚህ የገዛ መንገዳቸውን መረጡ፤ ነፍሳቸውም በርኩሰታቸው ደስ ይላታል፤
ማንም ሰው ማንኛውንም ርኩስ ነገር ማለትም የረከሰ አውሬ በድን፥ ወይም የረከሰ ከብት በድን፥ ወይም በደረቱ እየተሳበ የሚርመሰመስ የረከሰ ፍጥረት በድን ሳይታወቀው ቢነካ፥ እርሱ ርኩስ ይሆናል፤ በደለኛም ነው፤
ነገር ግን ከሚያመሰኩት ወይም ሰኰናቸው ከተሰነጠቀ እንስሳት መካከል ግመልን፥ ጥንቸልንና ሽኮኮን አትብሉ፤ ምክንያቱም እነርሱ ቢያመሰኩሁም፥ ሰኰናቸው አልተሰነጠቀምና እነዚህ ለእናንተ ርኩሶች ናቸው።