ዘዳግም 13:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አምላክህ ጌታ እንድትኖርባቸው ከሚሰጥህ ከተሞች በአንዲቱ ውስጥ እንዲህ ሲባል ብትሰማ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላክህ እግዚአብሔር እንድትኖርባቸው ከሚሰጥህ ከተሞች በአንዲቱ ውስጥ እንዲህ ሲባል ብትሰማ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እግዚአብሔር አምላክህ እንድትኖርባቸው ከሰጠህ ከተሞች በአንደኛዋ ውስጥ አንዳንድ ወራዶች ሰዎች ከመካከልህ ተነሥተው ነዋሪዎቹን ወደማታውቃቸው ወደ ሌሎች አማልክት ‘እንሂድና እናምልክ’ ብለው ወደ ጥፋት መንገድ መርተው መውሰዳቸውን ትሰማ ይሆናል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አምላክህ እግዚአብሔር ልትኖርባት ከሰጠህ ከተሞች በአንዲቱ ከተማህ፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላክህ እግዚአብሔር ልትኖርባት በሚሰጥህ በአንዲቱ ከተማህ፦ ክፋተኞች ሰዎች ከእናንተ ዘንድ ወጥተው፦ ሄደን የማታውቍቸውን ሌሎችን አማልክት እናምልክ ብለው የከተማቸውን ሰዎች አሳቱ ሲሉ ወሬ ብትሰማ፥ |
ከዚያም በኋላ የከተማዪቱ ሰዎች ሁሉ እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ይውገሩት፤ ክፉውንም ከመካከልህ አስወግድ፤ እስራኤልም ሁሉ ይህን ሰምቶ ይፈራል።