ሐዋርያት ሥራ 20:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተሰብስበንም በነበርንበት ሰገነት እጅግ መብራት ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በተሰበሰብንበትም ሰገነት ላይ ብዙ መብራት ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኛ በተሰበሰብንበት ፎቅ ብዙ መብራት ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተሰብስበን በነበርንበት ሰገነትም ብዙ መብራት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ተሰብስበንም በነበርንበት ሰገነት እጅግ መብራት ነበረ። |
በገቡም ጊዜ ወደሚኖሩበት ሰገነት ወጡ፤ ጴጥሮስና ዮሐንስም፥ ያዕቆብም፥ እንድርያስም፥ ፊልጶስም፥ ቶማስም፥ በርተሎሜዎስም፥ ማቴዎስም፥ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብም፥ ቀናተኛ የሚባለው ስምዖንም፥ የያዕቆብ ልጅ ይሁዳም።
አውጤኪስ የሚሉትም አንድ ጎበዝ በመስኮት ተቀምጦ ታላቅ እንቅልፍ አንቀላፍቶ ነበር፤ ጳውሎስም ነገርን ባስረዘመ ጊዜ እንቅልፍ ከብዶት ከሦስተኛው ደርብ ወደ ታች ወደቀ፤ ሞቶም አነሡት።