ሐዋርያት ሥራ 20:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 አውጤኪስ የሚሉትም አንድ ጎበዝ በመስኮት ተቀምጦ ታላቅ እንቅልፍ አንቀላፍቶ ነበር፤ ጳውሎስም ነገርን ባስረዘመ ጊዜ እንቅልፍ ከብዶት ከሦስተኛው ደርብ ወደ ታች ወደቀ፤ ሞቶም አነሡት። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም9 አውጤኪስ የተባለ አንድ ጐበዝም በመስኮት ላይ ተቀምጦ ነበር፤ ጳውሎስ ንግግሩን ባስረዘመ ጊዜ፣ እንቅልፍ እንቅልፍ አለውና ጭልጥ ብሎ ተኛ፤ ከሦስተኛውም ፎቅ ቍልቍል ወደቀ፤ ሞቶም አነሡት። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 ኤውጤኪስ የተባለ አንድ ወጣት በመስኮት ላይ ተቀምጦ ነበር፤ ጳውሎስ ንግግሩን በማስረዘሙ ወጣቱ ከባድ እንቅልፍ ያዘው፤ እንቅልፍ ስላሸነፈውም ከሦስተኛው ፎቅ ወደ ታች ወደቀ፤ ሰዎች ባነሡት ጊዜ ሞቶ አገኙት። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 ስሙ አውጤክስ የሚባል አንድ ጐልማሳ ልጅም በመስኮት በኩል ተቀምጦ ሳለ ከባድ እንቅልፍ አንቀላፍቶ ነበር፤ ጳውሎስም ትምህርቱን ባስረዘመ ጊዜ ያ ጐልማሳ ከእንቅልፉ ብዛት የተነሣ ከተኛበት ከሦስተኛው ፎቅ ወደ ታች ወደቀ፤ ሬሳውንም አነሡት። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 አውጤኪስ የሚሉትም አንድ ጎበዝ በመስኮት ተቀምጦ ታላቅ እንቅልፍ አንቀላፍቶ ነበር፤ ጳውሎስም ነገርን ባስረዘመ ጊዜ እንቅልፍ ከብዶት ከሦስተኛው ደርብ ወደ ታች ወደቀ፥ ሞቶም አነሡት። ምዕራፉን ተመልከት |