ሐዋርያት ሥራ 13:35 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደግሞ በሌላ ስፍራ “ቅዱስህን መበስበስን ያይ ዘንድ አትሰጠውም፤” ይላልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ በሌላም ስፍራ፣ “ ‘ቅዱስህ መበስበስን እንዲያይ አትፈቅድም’ ይላል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደግሞም በሌላ መዝሙር፥ ‘ቅዱሱ ልጅህ መበስበስ እንዲደርስበት አታደርገውም’ ይላል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሌላ ስፍራም እንዲህ ይላል፦ ‘ጻድቅህን መፍረስ መበስበስን ያይ ዘንድ አትሰጠውም።’ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞ በሌላ ስፍራ፦ ‘ቅዱስህን መበስበስን ያይ ዘንድ አትሰጠውም’ ይላልና። |
ሄኖክ ሞትን እንዳያይ በእምነት ተወሰደ፤ እግዚአብሔርም ስለ ወሰደው አልተገኘም። ከመወሰዱም በፊት እግዚአብሔርን ደስ እንዳሰኘ ተመስክሮለታል።