Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዮሐንስ 3:36 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

36 በልጁ የሚያምን የዘለዓለም ሕይወት አለው፤ ለልጁ የማይታዘዝ ግን የእግዚአብሔር ቁጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

36 በወልድ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት አለው፤ በወልድ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በላዩ ይሆናል እንጂ ሕይወትን አያይም።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

36 በወልድ የሚያምን የዘለዓለም ሕይወት አለው፤ በወልድ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቊጣ በእርሱ ላይ ይኖርበታል እንጂ ሕይወትን አያገኝም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

36 በወ​ልድ የሚ​ያ​ምን የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት አለው፤ በወ​ልድ የማ​ያ​ምን ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቍጣ መቅ​ሠ​ፍት በላዩ ይኖ​ራል እንጂ ሕይ​ወ​ትን አያ​ይም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

36 በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮሐንስ 3:36
38 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘለዓለም ሕይወት አለው፤ ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም።


ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑ ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች የሚሆኑበትን ሥልጣን ሰጣቸው፤


እግዚአብሔር በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል መዳንን እንድናገኝ እንጂ ለቁጣ እንድንሆን አስቀድሞ አልመረጠንም።


ከዚህ የተነሣ በማይታዘዙት ልጆች ላይ የእግዚአብሔር ቁጣ ይመጣልና ማንም በከንቱ ንግግር አያታላችሁ።


እንግዲህ አሁን በደሙ ከጸደቅን ይበልጡንም በእርሱ በኩል ከቁጣ እንድናለን።


እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ ቃሌን የሚጠብቅ ቢኖር ለዘለዓለም ሞትን አያይም።”


እኔም የዘለዓለም ሕይወትን እሰጣቸዋለሁ፤ ለዘለዓለምም አይጠፉም፤ ከእጄም ማንም አይነጥቃቸውም።


ኢየሱስም መልሶ “እውነት እውነት እልሃለሁ፤ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም፤” አለው።


ነገር ግን የሚፈሩ፥ የማያምኑ፥ የሚረክሱ፥ ነፍሰ የሚያጠፉ፥ የሚሴሰኑ፥ አስማትን የሚያደርጉ፥ ጣዖትንም የሚያመልኩና የሚዋሹ ሁሉ ዕጣ ክፍላቸው በዲንና በእሳት በሚቃጠል ባሕር ውስጥ ነው፤ ይህም ሁለተኛው ሞት ነው።”


እንዲሁም ከሚመጣው ቁጣ ያዳነንን ኢየሱስን፥ እርሱ ከሞት ያስነሣውን ልጁን፥ ከመንግሥተ ስማይ እንዴት እንደምትጠብቁ ይናገራሉ።


‘ከግብጽ የወጡት ዕድሜአቸው ሀያ ዓመት የሞላቸውና ከዚያም በላይ ያሉት ሰዎች እኔን ፈጽመው አልተከተሉምና ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም ለመስጠት የማልሁላቸውን ምድር አያዩም፤


ከሕግ ሥራ የሆኑት ሁሉ ከርግማን በታች ናቸው፤ “በሕግ መጽሐፍ በተጻፉት ሁሉ የማይኖርና የማይፈጽማቸው ሁሉ የተረገመ ይሁን፤” ተብሎ ተጽፎአልና።


ስለዚህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኩነኔ የለባቸውም።


ሥጋም የለበሰ ሁሉ የእግዚአብሔርን ማዳን ይይ፤”


በሕይወቱ ሳለ ነፍሱን ባርኮአልና ለሰውነቱ መልካም በማድረጉ ይወደሳልና።


ከቤትህ ሙላት ይጠግባሉ፥ ከተድላህም ፈሳሽ ታጠጣቸዋለህ።


እንግዲህ የእግዚአብሔርን ልጅ የረገጠ፥ የተቀደሰበትን ያንን የኪዳኑን ደም እንደ ርኩስ ነገር የቆጠረ፥ የጸጋውንም መንፈስ ያስቆጣ፥ ቅጣቱ እጅግ የከፋ እንዴት የማይሆን ይመስላችኋል?


እኛስ እንዲህ ያለውን ታላቅ መዳን ቸል ብንለው፥ እንዴት እናመልጣለን? ይህ በጌታ በመጀመሪያ የተነገረ ነበርና፥ የሰሙትም ለእኛ ይህንኑ አረጋግጠውልናል።


እነሆ፥ እርሱ ኮርቶአል፥ ነፍሱ በውስጡ ቅን አይደለችም፤ ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል።


ተግሣጹን ተቀበሉ ጌታ እንዳይቈጣ እናንተም በመንገድ እንዳትጠፉ፥ ቁጣው ፈጥና ትነድዳለችና። በእርሱ የታመኑ ሁሉ የተመሰገኑ ናቸው።


ነፍሴ ወደ መቃብር እንዳትወርድ አድኖአታል፥ ሕይወቴም ብርሃንን ታያለች ይላል።”


ሕጉ መቅሠፍትን ያስከትላልና፤ ነገር ግን ሕግ በሌለበት መተላለፍ የለም።


ዐይኖቼ ማዳንህን አይተዋልና፤


እነዚህ ወደ ዘለዓለም ቅጣት፥ ጻድቃን ግን ወደ ዘለዓለም ሕይወት ይሄዳሉ።”


ያመነና የተጠመቀ ይድናል፤ ያላመነ ግን ይፈረድበታል።


የሚያጭድ ደመወዝን ይቀበላል፤ የሚዘራና የሚያጭድም አብረው ደስ እንዲላቸው ለዘለዓለም ሕይወት ፍሬን ይሰበስባል።


ከሰማይ የወረደው እንጀራ ይህ ነው፤ አባቶቻችሁ በልተው ነገር ግን እንደሞቱበት ዓይነት አይደለም፤ ይህን እንጀራ የሚበላ ለዘለዓለም ይኖራል።”


ያላመኑት አይሁድ ግን የአሕዛብን ልብ በወንድሞች ላይ አነሣሡ፤ አስከፉም።


ካልታዘዙትም በስተቀር፥ ወደ እረፍቱ እንዳይገቡ የማለባቸው እነማን ነበሩ?


እንግዲህ ባለማመናቸው ጠንቅ ሊገቡ እንዳልተቻላቸው እናያለን።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች