ቶዒ ከሀዳድዔዜር ጋር ሁልጊዜ ይዋጋ ስለ ነበር፥ ልጁን ዮራምን ወደ ንጉሥ ዳዊት ለሰላምታና በሀዳድዔዜር ላይ ሰለተቀዳጀውም ድል ደስታውን እንዲያቀርብለት ላከው፤ ልጁም የብር፥ የወርቅና የናስ ዕቃ ይዞ መጣ።
2 ሳሙኤል 8:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሐማት ንጉሥ ቶዒ ዳዊት መላውን የሀዳድዔዜርን ሠራዊት ማሸነፉን በሰማ ጊዜ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሐማት ንጉሥ ቶዑ፣ ዳዊት መላውን የአድርአዛርን ሰራዊት ማሸነፉን በሰማ ጊዜ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሐማት ንጉሥ ቶዒ ዳዊት የሀዳድዔዜርን ሠራዊት በሙሉ ድል ማድረጉን ሰማ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሓማትም ንጉሥ ታይ ዳዊት የአድርአዛርን ጭፍራ ሁሉ እንደ መታ ሰማ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሐማትም ንጉሥ ቶዑ ዳዊት የአድርአዛርን ጭፍራ ሁሉ እንደ መታ ሰማ። |
ቶዒ ከሀዳድዔዜር ጋር ሁልጊዜ ይዋጋ ስለ ነበር፥ ልጁን ዮራምን ወደ ንጉሥ ዳዊት ለሰላምታና በሀዳድዔዜር ላይ ሰለተቀዳጀውም ድል ደስታውን እንዲያቀርብለት ላከው፤ ልጁም የብር፥ የወርቅና የናስ ዕቃ ይዞ መጣ።
በዚያም በቤተ መቅደሱ ሰሎሞንና የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ሰባት ቀን ሙሉ የዳስ በዓል አክብረው ሰነበቱ፤ በስተ ሰሜን ከሐማት መተላለፊያ አንሥቶ በስተ ደቡብ እስከ ግብጽ ድንበር ድረስ ካለው ምድር ሁሉ የመጣው ሕዝብ እጅግ ብዙ ነበር።
ወደ ካልኔ እለፉና ተመልከቱ፤ ከዚያም ወደ ታላቂቱ ሐማት ሂዱ፤ ከዚያም ወደ ፍልስጥኤም ጌት ውረዱ፤ እነርሱ ከእነዚህ መንግሥታት ይሻላሉን? ወይስ ድንበራቸው ከድንበራችሁ ይሰፋልን?