እንደገና በፍልስጥኤማውያንና በእስራኤል መካከል ጦርነት ተደረገ። ዳዊትም ከሰዎቹ ጋር ሆኖ ፍልስጥኤማውያንን ለመውጋት ወረደ፤ ዳዊትም ደከመው።
2 ሳሙኤል 5:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊት በእስራኤል ላይ ንጉሥ ሆኖ መቀባቱን ፍልስጥኤማውያን በሰሙ ጊዜ፥ ፍልስጤማውያን ሁሉ ዳዊትን ለመፈለግ በሙሉ ኀይላቸው ወጡ፤ ዳዊት ግን ይህን ሰምቶ ወደ ምሽጉ ወረደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊት በእስራኤል ሁሉ ላይ ንጉሥ ሆኖ መቀባቱን ፍልስጥኤማውያን በሰሙ ጊዜ፣ እርሱን ፍለጋ በሙሉ ኀይላቸው ወጡ፤ ዳዊትም ይህን ሰምቶ ወደ ምሽጉ ወረደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊት በእስራኤል ላይ መንገሡን ፍልስጥኤማውያን ሰሙ፤ ስለዚህም ሠራዊታቸው ዳዊትን ለመማረክ ገሥግሦ ሄደ፤ ዳዊት የእነርሱን መምጣት በሰማ ጊዜ ወደ ተመሸገ ስፍራ ወረደ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፍልስጥኤማውያንም ዳዊት በእስራኤል ላይ ንጉሥ ሆኖ እንደ ተቀባ ሰሙ፤ ፍልስጥኤማውያንም ሁሉ ዳዊትን ሊፈልጉ ወጡ፤ ዳዊትም በሰማ ጊዜ ወደ ምሽጉ ወረደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፍልስጥኤማውያንም ዳዊት በእስራኤል ላይ ንጉሥ ሆኖ እንደ ተቀባ ሰሙ፥ ፍልስጥኤማውያንም ሁሉ ዳዊትን ሊፈልጉ ወጡ፥ ዳዊትም በሰማ ጊዜ ወደ ምሽጉ ወረደ። |
እንደገና በፍልስጥኤማውያንና በእስራኤል መካከል ጦርነት ተደረገ። ዳዊትም ከሰዎቹ ጋር ሆኖ ፍልስጥኤማውያንን ለመውጋት ወረደ፤ ዳዊትም ደከመው።
ከዚህ በኋላ ዳዊት ፍልስጥኤማውያንን ድል አደረጋቸው፤ በቁጥጥሩም ሥር አደረጋቸው፥ ሜተግ አማ የተባለችውንም ከተማ ዳዊት ከፍልስጥኤማውያን እጅ ወሰደ።
የገበሩትም መንግሥታት ኤዶምና ሞዓብ፥ አሞናውያን፥ ፍልስጥኤማውያንና አማሌቃውያን ነበሩ። እንዲሁም ከጾባ ንጉሥ ከረሖብ ልጅ ከሀዳድዔዜር የወሰደውን ምርኮ ለጌታ ቀደሰ።