የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




2 ሳሙኤል 24:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሆኖም የንጉሡ ቃል ኢዮአብንና የሠራዊቱን አዛዦች አሸነፋቸው፤ ስለዚህ የእስራኤልን ሕዝብ ለመቁጠር ከፊቱ ወጥተው ሄዱ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሆኖም የንጉሡ ቃል ኢዮአብንና የሰራዊቱን አዛዦች ስላሸነፋቸው፣ የእስራኤልን ሰራዊት ለመመዝገብ ከፊቱ ወጥተው ሄዱ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ንጉሡ ግን ኢዮአብና የጦር መኰንኖቹ ትእዛዙን እንዲፈጽሙ ስላስገደዳቸው ከፊቱ ወጥተው የእስራኤልን ሕዝብ ለመቊጠር ሄዱ።

ምዕራፉን ተመልከት

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ነገር ግን የን​ጉሡ ቃል በኢ​ዮ​አ​ብና በሠ​ራ​ዊቱ አለ​ቆች ላይ አሸ​ነፈ። ኢዮ​አ​ብና የሠ​ራ​ዊቱ አለ​ቆ​ችም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ሕዝብ ይቈ​ጥሩ ዘንድ ከን​ጉሥ ዘንድ ወጡ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ነገር ግን የንጉሡ ቃል በኢዮአብና በሠራዊቱ አለቆች ላይ አሸነፈ። ኢዮአብና የሠራዊቱ አለቆችም የእስራኤልን ሕዝብ ይቆጥሩ ዘንድ ከንጉሥ ዘንድ ወጡ።

ምዕራፉን ተመልከት



2 ሳሙኤል 24:4
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኢዮአብ ግን ንጉሡን፥ “ጌታ አምላክህ ሕዝቡን መቶ ዕጥፍ ያድርገው፤ የጌታዬ የንጉሡ ዐይን ይህን ለማየት ያብቃው፤ ንጉሡ ጌታዬ ግን ይህን ለማድረግ የፈለገው ለምንድን ነው?” ሲል መለሰለት።


ዮርዳኖስን ከተሻገሩ በኋላ፥ በሸለቆው ውስጥ ካለችው ከተማ በስተ ደቡብ በምትገኘው በአሮዔር አጠገብ ሰፈሩ፤ ከዚያም በጋድ በኩል አድርገው ወደ ያእዜር ሄዱ፤


ነገር ግን የንጉሡ ቃል በኢዮአብ ላይ አሸነፈ፤ ኢዮአብም ወጥቶ በእስራኤል ሁሉ ላይ ተዘዋወረ፥ ወደ ኢየሩሳሌምም ተመለሰ።


አዋላጆቹ ግን እግዚአብሔርን ፈሩ፥ የግብጽ ንጉሥም እንዳዘዛቸው አላደረጉም፥ ወንዶቹን ሕፃናትንም በሕይወት ይኖሩ ዘንድ ተዋቸው።


“አንተ የእስራኤልን ልጆች ቍጥር ተቀብለህ በቆጠርሃቸው ጊዜ መቅሰፍት እንዳይሆንባቸው፥ በቆጠርሃቸው ጊዜ ከእነርሱ ሰው ሁሉ እንደ ቁጥራቸው መጠን የነፍሱን ቤዛ ለእግዚአብሔር ይስጥ።


የንጉሥ ቃል ኃይለኛ ነውና፥ “ይህንስ ለምን ታደርጋለህ?” ማን ይለዋል?


ጴጥሮስና ሐዋርያትም መልሰው አሉ “ከሰው ሥልጣን ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባል።