ዓይኑንም አነሣና እነሆ፥ ሦስት ሰዎች በፊቱ ቆመው አየ፥ ባያቸውም ጊዜ ሊቀበላቸው ከድንኳኑ ደጃፍ ተነሥቶ ሮጠ፥ ወደ ምድርም ሰገደ፥ እንዲህም አለ፦
2 ሳሙኤል 24:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኦርናም ቁልቁል ሲመለከት፥ ንጉሡና አገልጋዮቹ ወደ እርሱ ሲመጡ አየ፤ ኦርናም ወጥቶ በንጉሡ ፊት በምድር ላይ በግምባሩ ተደፋ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኦርናም ቀና ብሎ ንጉሡና ሰዎቹ ወደ እርሱ ሲመጡ አየ፤ ከዚያም ወጥቶ ወደ መሬት ለጥ ብሎ ለንጉሡ እጅ ነሣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኦርናም ወደ ታች ሲመለከት ንጉሥ ዳዊትና ባለሟሎቹ የሆኑት ባለሥልጣኖች ወደ እርሱ ሲመጡ አየ፤ እርሱም በዳዊት ፊት ለጥ ብሎ እጅ ነሣ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኦርናም ሲመለከት ንጉሡና ብላቴናዎቹ ወደ እርሱ ሲመጡ አየ፤ ኦርናም ወጥቶ በንጉሡ ፊት በምድር ላይ በግንባሩ ሰገደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኦርናም ሲመለከት ንጉሡና ባሪያዎቹ ወደ እርሱ ሲመጡ አየ፥ ኦርናም ወጥቶ በንጉሡ ፊት በምድር ላይ በግምባሩ ተደፋ። |
ዓይኑንም አነሣና እነሆ፥ ሦስት ሰዎች በፊቱ ቆመው አየ፥ ባያቸውም ጊዜ ሊቀበላቸው ከድንኳኑ ደጃፍ ተነሥቶ ሮጠ፥ ወደ ምድርም ሰገደ፥ እንዲህም አለ፦
በሦስተኛውም ቀን፥ እነሆ፥ የተቀደደ ልብስ የለበሰ፥ በራሱም ላይ ትቢያ የነሰነሰ አንድ ሰው ከሳኦል ሰፈር መጣ። ወደ ዳዊት መጥቶም በግምባሩ በመደፋት እጅ ነሣ።
ኦርናም፥ “ንጉሥ ጌታዬ ወደ አገልጋዩ የመጣው ለምንድን ነው?” አለ። ዳዊትም፥ “መቅሠፍቱ ከሕዝቡ እንዲከለከል ለጌታ መሠዊያ እንድሠራ ዐውድማህን ልገዛ ነው” ሲል መለሰለት።