2 ሳሙኤል 22:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በፊቱ ያለ ነውር ነበርሁ፤ ራሴንም ከኃጢአት ጠብቄአለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በፊቱ ነቀፋ አልነበረብኝም፤ ራሴንም ከኀጢአት ጠብቄአለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእርሱ ዘንድ ንጹሕ ነበርኩ፥ ከኃጢአትም ራሴን ጠብቄአለሁ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእርሱ ዘንድ ንጹሕ እሆናለሁ፤ ከዐመፃዬም ራሴን እጠብቃለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእርሱ ዘንድ ቅን ነበርሁ፥ ከኃጢአቴም ተጠበቅሁ። |
ጌታም ኖኅን እንዲህ አለው፦ “በዚህ ዘመን ካለው ትውልድ መካከል ጻድቅ አንተ ሆነህ አይቼሃለሁና፥ አንተ ቤተሰቦችህን ሁሉ ይዘህ ወደ መርከብ ግባ።
እንግዲህ የጌታን ፍርሃት አውቀን፥ ሰዎችን ለማስረዳት እንጥራለን፤ ስለ ራሳችን ከሆነ በእግዚአብሔር ዘንድ የተገለጥን ነን፤ ለእናንተም ሕሊና የተገለጥን እንደ ሆንን ተስፋ አደርጋለሁ።
እንግዲህ እነደዚህ ዓይነት ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ማንኛውንም ሸክምና የተጣበቅንበትን ኅጢአት ሁሉ አራግፈን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በጽናት እንሩጥ።