2 ሳሙኤል 2:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህ ጊዜ የሳኦል ሠራዊት አዛዥ የኔር ልጅ አበኔር፥ የሳኦልን ልጅ ኢያቡስቴን ወስዶ ወደ ማሕናይም አሻገረው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ የሳኦል ሰራዊት አዛዥ የኔር ልጅ አበኔር፣ የሳኦልን ልጅ ኢያቡስቴን ወስዶ ወደ መሃናይም አሻገረው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሳኦል ሠራዊት አዛዥ የኔር ልጅ አበኔር ከሳኦል ልጅ ከኢያቡስቴ ጋር የዮርዳኖስን ወንዝ በመሻገር ወደ ማሕናይም ሸሽቶ ሄደ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሳኦልም ጭፍራ አለቃ የኔር ልጅ አበኔር የሳኦልን ልጅ ኢያቡስቴን ወስዶ ከሰፈር ወደ መሃናይም አወጣው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሳኦልም ጭፍራ አለቃ የኔር ልጅ አበኔር የሳኦልን ልጅ ኢያቡስቴን ወስዶ ወደ መሃናይም አሻገረው፥ |
የሳኦልም ወንድሞች ከሆኑ ከብንያም ልጆች የሚበልጠው ክፍል እስከዚያ ዘመን ድረስ የሳኦልን ቤት ይከተል ነበርና ከእነርሱ ዘንድ የመጡ ሦስት ሺህ ነበሩ።
ዳዊት ፍልስጥኤማዊውን ለመግጠም ሲሄድ ሳኦል ተመልክቶ የሠራዊቱን አዛዥ አበኔርን፥ “አበኔር ሆይ፤ ይህ ልጅ የማን ነው?” ሲል ጠየቀው። አበኔርም፥ “ንጉሥ ሆይ፤ በሕያው ነፍስህ እምላለሁ፤ አላውቅም” ብሎ መለሰለት።
ዳዊት ሠራዊቱንና የኔርን ልጅ አቤኔርን፥ “አቤኔር ሆይ፥ አትመልስልኝምን?” ሲል ተጣራ። አቤኔርም፥ “በንጉሡ ላይ የምትጮኽ አንተ ማነህ?” በማለት መለሰ።