2 ሳሙኤል 2:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤኔርን ለመያዝ ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ ሳይል ተከተለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሣሄልም ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ ሳይል አበኔርን ተከታተለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አበኔርን አባሮ ለመያዝ በቀጥታ ወደ እርሱ ሮጠ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሣሄልም የአበኔርን ፍለጋ ተከታተለ፤ አበኔርንም ከማሳደድ ቀኝና ግራ አላለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሣሄልም የአበኔርን ፍለጋ ተከታተለ፥ አበኔርንም ከማሳደድ ቀኝና ግራ አላለም። |
ከዚያም አበኔር፥ “ወደ ቀኝህ ወይም ወደ ግራህ ዘወር በልና አንዱን ጎልማሳ ይዘህ ምርኮውን ውሰድ” አለው። አሣሄል ግን እርሱን ማሳደዱን ቀጠለ።
አበኔርም ወደ ኬብሮን በተመለሰ ጊዜ፥ ኢዮአብ ለብቻው የሚያነጋግረው በመምሰል ወደ ቅጽሩ በር ይዞት ሄደ፤ እዚያም የወንድሙን የአሣሄልን ደም ለመበቀል ሆዱ ላይ ወግቶ ገደለው።
ኢዮስያስ የቀድሞ አባቱን የዳዊትን መልካም ምሳሌነት በመከተልና ለእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ታዛዥ በመሆን፥ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሥራ ሠራ።
ነገር ግን ጽና፥ እጅግም በርታ፤ ባርያዬ ሙሴ ያዘዘህን ሕግ ሁሉ ጠብቅ፥ አድርገውም፤ በምትሄድበትም ሁሉ እንዲከናወንልህ ከእርሱ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አትበል።